'የጥቁር ባህር እህል ስምምነት' በቅርቡ እንደሚታደስ ፕሬዝደንት ኢርዶጋን ተናገሩ
የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሮ ኩሌባዩክሬን አቋሟን አትቀይርም ብለዋል
ኢርዶጋን እንዳሉት ከሩሲያ ጋር የሚደረጉ ንግግሮች ግባራዊ እንዲሆኑ ዩክሬንም አቋሞቿን ማለዘብ አለባት ሲሉተናግረዋል
የቱርኩ ፕሬጥቁርት ሬስፕ ታይፕ ኢርዶጋን 'የጥቁር ባህር የእህል ስምምነት' በቅርቡ እንደሚታደስ ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ከተወያዩ በኋላ እንደተናገሩት ዩክሬን እህሏን በጥቁር ባህር በኩል ወደ ውጭ እንድትልክ የሚያስችላት ስምምነት በቅርቡ ሊታደስ ይችላል ብለዋል።
ተመድ የዚህ ስምምነት መታደስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የምግብ እጥረት ችግር ያቃልለዋል ብሏል።
ሩሲያ ባለፈው ሐምሌ በተመድ እና በቱርክ አማካኝነት ከተደረሰው ስምምነት የወጣችው የራሷ እህል እና ማዳበሪያ ወደ ውጭ ለማስወጣት እንቅፋት እንደገጠማት ነው።
ቀደም ሲል ስምምነቱ እንዲደረስ ሚና የነበራቸው ኢርዶጋን እና ተመድ ስምምነቱ እንዲታደስ ፑቲን እያግባቡ ይገኛሉ።
ኢርዶጋን በሩሲያ የጥቁር ባህር ከተማ ሶቺ እንደተናገሩት ቱርክ በቅርቡ መፍትሄ ይመጣል ብላ እንደምትጠብቅ ገልጸዋል።
ሩሲያ የምትጠብቀው የታወቀ ነው ያሉት ኢርዶጋን የስምምነቱን ውስንነቶች እንዲቀረፉ እንዲሁም ቱርክ እና ተመድ የሩሲያን ስጋት የሚቀንስ የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባሉ ብለዋል።
ኢርዶጋን እንዳሉት ከሩሲያ ጋር የሚደረጉ ንግግሮች ግባራዊ እንዲሆኑ ዩክሬንም አቋሞቿን ማለዘብ አለባት ሲሉተናግረዋል።
ነገርግን የዩክሬን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲምትሮ ኩሌባዩክሬን አቋሟን አትቀይርም ብለዋል።