ፕሬዝደንት ኤርዶጋን “ታሪክን በደንብ ተማር” ሲሉ ፕሬዝደንት ባይደን ስለአርመን የተናገሩትን ተቃወሙ
በቱርክ የሚገኙ አርመኖች በመጀመሪያው የአለም ጦርነት የደረሰባቸውን መጥፎ ሁኔታ በቱርክ ተሰባስበው አስበዋል
ኤርዶጋን፤ ፕሬዝደንት ባይደን በፈረንጆቹ በ1915 በአርመን የተካደውን ክስተት ለሁለተኛ ጊዜ የ“ዘርማጥፋት” ድርጊት ነው ብለው መግለጻቸውን ተቃውመዋል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን፤ ፕሬዝደንት ባይደን በፈረንጆቹ በ1915 በአርመን የተካደውን ክስተት ለሁለተኛ ጊዜ የ“ዘርማጥፋት” ድርጊት ነው ብለው መግለጻቸውን ተቃውመዋል፡፡
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ይህን ያሉት በቱርክ በፕሬዝዳንት ቤተመንግስት የነበረውን ስብሰባ በመሩበት ወቅት ነው፡፡
በአርመኒያ ተደርጓል ስለተባለው ወንጀላ፤በጥቂት ሀገራት እና ፓርላመንቶች የሚሰጠው አስተያያት በቱርክ መንግስት ተቀባይነት የለውም ያሉት ፕሬዝደንቱ ፕሬዝደንት ባይደን ለ1915 የአርመን ክስተት በውሸት እና በሃሰተኛ መረዳ ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል፡፡
“ ባይደን ታሪክን በደንብ መማር አለበት፤ ይህ ሳያውቅ ቱርክን ለመከራከር መሞከሩን ይቅር አንለውም “
የአርመን ሰዎች በዚህ የአርመንን እና የቱርክ ህዝብን ለማጋጨት አላማው ባደረገው ግብዝ አመለካከት ሲጎዱ ነበር፤ይጎዳሉም ብለዋል ፕሬዝደንጽ ኤርዶጋን፡፡
በቱርክ እና በአርመን መካከል ያለፈ ቁርሾ ከማጋነን ይልቅ ሰለማዊ ግንኙት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ኤርዶጋን የቱርክ ላሉት የአርመን ፓትሪያሪክ መልእክት መላካቸውን የቱርክ ፕሬዝደንት ቢሮ የኮሙነኬሽን ክፍል አስታውቋል፡፡
በቱርክ የሚገኙ አርመኖች በመጀመሪያው የአለም ጦርነት የደረሰባቸውን መጥፎ ሁኔታ በቱርክ ተሰባስበው አስበዋል፡፡