የአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ባለፈው ሳምንት በቱርክ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሪሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን በመጨው የካቲት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን (ዩኤኢ) የመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው ተነገረ፡፡
ፕሬዝዳንቱ ከቱርኬሚስታን ጉብኝት ከተመለሱ በኋላ በወጣ መግለጫ፤ በቱርክ አንካራ ከዩኤኢ ጋር የተደረገው ስምምነት በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ታሪካዊ ነው ተብሏል፡፡ ፕሬዝዳንቱ የአቡዳቢ አልጋወራሽና ምክትል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መሀመድ ቢን ዛይድን በቱርክ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት አዲስ የግንኙት ምእራፍ መሰረት ጥሏል ተብሏል፡፡
በፈረንጆቹ 2011 ከመሀመድ ቢን ዛይድ ጋር መገናኘታቸውን የገለጹት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን፤”ከዚያ በኋላ የተለያዩ ጊዜያት አሳልፈናል፤ነገርግን የግንኙነት ገመዱን ሙሉበሙሉ አልበጠስንም” ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የሁለቱ ሀገራት ደህንነቶች እርስበእርሳቸው ሲነጋገሩ ነበር፤ በዘህም የንግድ ግንኙነታቸውን ቀጥሏልም ብለዋል፡፡
የቱርክ ፕሬዝዳንት ንግግራቸውን በመቀጠል “በእርግጥም ይህ ጉብኝት (የሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ጉብኝትን በተመለከተ) በቤተሰብ ስሜት ነበር። በዚህ ጉብኝት እነዚህን ስምምነቶች ጨርሰናል ብለዋል ኤርዶጋን፡፡
በዚህ ስምምነት ጽሑፍ ውስጥ የተካተቱት ጹሁፎች በቱርክ እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መካከል አዲስ ዘመን እንዲጀምር እና ዘላቂ እንዲሆን ያደረገ እርምጃ ነው ብዬ አምናለሁ ።
“በሁለትዮሽ እና በልዑካን መካከል የተካሄዱት ስብሰባዎች በጥሩ ሁኔታ የተከናወኑ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ለቀጣዩ እርምጃ እድል ካለ በሚቀጥለው የካቲት ሌላ ጉብኝት አደርጋለሁ፣ ከብዙ የልዑካን ቡድን ጋር ለመሄድ ተስፋ አደርጋለሁ እና አንዳንድ እርምጃዎችን በጥብቅ እንወስዳለን”ብለዋል ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን።
ኤርዶጋን "በ (ቱርክ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ኃላፊ ጉብኝቶች እንደሚኖሩ" ተናግረዋል፡፡ ባለፈው ረቡዕ የአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በቱርክ ያደረጉት ውጤታማ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ስትራቴጂካዊ ስምምነት እንዲፈረም አስላችሏል፡፡