የቱርኩ ፕሬዝዳንት የሩሲያው አቻቸው ፑቲን ጋር ለመምከር ሶቺ ገብተዋል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሃን ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው ሩሲያ የገቡት
የሞስኮና አንካራ ግንኙነት በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በወታደራዊና ንግድ ዘርፎች እያደገ መምጣቱን መሪዎቹ አስታውቀዋል
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሃን ለአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሩሲያ መግባታቸውን ጽህፈት ቤታቸው አስታወቀ።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም የቱርክ አቻቸውን በጥቁር ባሕር ላይ በምትገኘው የሶቺ ከተማ ተቀብለዋቸዋል።
ረሲፕ ታኢብ ኤርዶሃን የሩሲያ አቻቸው በችግር ጊዜ ስለደረሱላቸው ምስጋና አቅርበዋል፤ የሞስኮና አንካራ ግንኙነት በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በወታደራዊ እና ንግድ ዘርፎች እያደገ መምጣቱን መሪዎቹ በሩሲያ እያደረጉት ባለው ውይይት ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን በሀገራቸው ያለው የቱርክ ኢንቨስትመንት 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር መድረሱን እና በቱርክ ያለው የሩሲያ ኢንቨስትመንት 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ገልጸዋል።
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሃን የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል።የሀገራቱ ግንኑኘት ከዚህ በላይም ሊያድግ እንደሚችል የቱርኩ ፕሬዝዳንት እምነታቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ለቱርክ የቱሪዝም ዘርፍ ድጋፍ ማድረጋቸውን ያነሱት ኤርዶሃን፤ ሩሲያውያን ቱርክን ስለሚመርጡም እንደሚያመሰግኑ አስታውቀዋል፡፡
ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሃን የአኩዩ ኒዩክለር ማብላያ ጣቢያ በተያዘለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ ገልጸው ለዚህም 10 ሺ የቱርክ እንዲሁም ሶስት ሺ የሩሲያ ባለሙያዎች ስራውን እያከናወኑ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የአኩዩ ኒዩክለር ማብላያ ጣቢያ በሚቀጥለው ዓመትም የመጀመሪያው ዩኒት እንደሚጠናቀቅ የገለጹት የቱርኩ ፕሬዝዳንት በዚህ ጣቢ ለይ የሚሰቱት ሁሉም ሰራተኞች በሩሲያ መሰልጠናቸውን ገልጸዋል። ይህም የሞስኮ እና አንካራ ግንኙነት ማደግ ምስሌ ነው ብለዋል።
ሞስኮ እና አንካራ በወታደራዊ መስክ ከጀመሩት የጋራ እርምጃ ማስቆም እንደማይቻልም የቱርኩ ፕሬዝዳንት ገልጸው በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይም ትኩረት ሰጥተው የተናገሩት በሩሲያና ቱርክ ግንኑነት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።