“የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ወደ ኦልድትራፎርድ ለማምጣት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋልን” - ቴንሃግ
በኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታን ማንቸስተር ዩናይትድ ከማንቸስተር ሲቲ ይጫወታሉ
አሰልጣኝ ቴንሃግ የማንቸስተር ዩናይትድ ዳጋፊዎችን “የዓለማችን ምርጡ ደጋፊዎች ናችሁ” ብለዋል
የማንቸስተር ዩናትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ “የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ወደ ኦልድትራፎርድ ለማምጣት የምንችለውን ሁሉ እናደርጋልን” ብለዋል።
ማንቸስተር ዩናትድ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የውድድር አመቱ የመጨረሻ ጨዋታውን ትናንት ምሽት ከኒውካስል ጋር አድርጓል።
በ34ኛ ሳምንት ተስተካካይ የጨዋታ መርሃ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
በጨዋታው ላይ ኮቢ ማይኖ ፣ አማድ ዲያሎ እና ራስሙስ ሆይሉንድ የማንቸስተር ዩናትድን የማሸነፊያ ግቦች መከረብ ያሳረፉ ሲሆን፤ ለኒውካስል ዩናይትድ ከመሸነፍ ያላዳኑትን ሁለት ግቦች አንቶኒ ጎርደን እና ሀል አስቆጥረዋል።
ጨዋታውን መጠናቀቅ ተከትሎም ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም ለተገኙ የክለቡ ደጋፊወች ንግግር አድርገዋል።
አሰልጣኙ በንግግራቸውም የማንቸስተር ዩናይትድ ዳጋፊዎችን “የዓለማችን ምርጡ ደጋፊዎች ናችሁ” ያሉ ሲሆን፤ “የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን እናመጣላቹዋለን” ብለዋል።
“የውድድር ዓመቱ ገና አላለቀም ወሳኝ ጨዋታዎች አሉን” ያሉት አሰልጣኙ፤ “አሁን ጉዞዋችን ለኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ዊምብሌይ ይሆናል” ሲሉም ተናግረዋል።
የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ኢንዲዘጋጁም አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ ጥሪ አቅርበዋል።
የኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜ ጨዋታን ለማሸነፍ መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት አሰልጣኝ ቴንሃግ፤ “የዩናትድ ተጨዋቾች ጨዋታውን አሸንፈው ዋንጫውን ወደ ኦልድትራፎርድ ለማምጣት ያላቸውን ሁሉ እንደሚሰጡ ቃል እገባለሁ” ብለዋል።
የዘንድሮ የኤፍኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ በማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ መካከል ቅዳሜ, ግንቦት 17 በዊንብሌይ ስታዲየም ይካሄዳል።
ማንችስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር አመት ሰ84ማንያ አራት ግቦች ሲቆጠሩባቸው ከ30 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተነግሯ።
ማቸስተር ዩናትድ በፕሪምየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 57 ነጥቦችን በመሰብሰብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።