በረራው በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያ ነው ተቋርጦ የነበረው
ኤርትራ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አቁማው የነበረውን ዓለም አቀፍ በረራ በድጋሚ ልትጀምር ነው።
የኤርትራ ትራንስፖርት እና ኮሙንኬሽን ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ መሰረት በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ወደ ሀገሯ እና ከአስመራ ወደ ሌሎች ሀገራት ይደረጉ የነበሩ በረራዎችን አግዳ ነበር።
በዚህም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባም ሆነ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚደረጉ በረራዎች አልነበሩም፡፡
አሁን ግን በረራዎቹ ዳግም መጀመራቸው ተገልጿል።
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በሳምንት ሁለት ቀናት ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ዱባይ በረራዎች ይደረጋሉም ነው ያለው ሚኒስቴሩ በመግለጫው።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከ20 ዓመታት በላይ ምንም አይነት የትራንስፖርት ግንኙነት ያልነበራቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በ2011 ዓ.ም የአየር ትራንስፖርት መጀመራቸው ይታወሳል።
በኤርትራ 3 ሺ 334 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን 10 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ ጆንሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ መረጃ ያስረዳል።