ትራምፕ እስራኤል ጦርነቱን እንድታቆም ይነግሯታል የሚል ተስፋ አለኝ- የቱርኩ ኢርዶጋን
ፕሬዝደንቱ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቆም ጥሩ ጅምር ሊሆን እንደሚችልም አስተያየት መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኢርዶጋን ከትራምፕ ጋር በስልክ ማውራታቸውን እና ቱርክን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን ተናግረዋል
የቱርኩ ፕሬዝደንት ታይፕ ኢርዶጋን በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ጦርነት እንድታቆም ይነግሯታል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ባዛሬው እለት ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቱ ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቆም ጥሩ ጅምር ሊሆን እንደሚችልም አስተያየት መስጠታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
- እስራኤል በሽብር ክስ የተፈረደባቸው ሰዎች ቤተሰቦችን ከሀገሪቱ የሚያባርር ህግ አጸደቀች
- እስራኤል የዜጎቿን ህይወት ለመታደግ ወደ ኔዘርላንድ አውሮፕላኖች ልትልክ መሆኑን አስታወቀች
"ትርምፕ ግጭቶችን ለማቆም ቃል ገብተዋል...ያ ቃል እንዲፈጸም እና እስራኤል ጦርነት እንድታቆም እንዲነገራት እንፈልጋለን"ብለዋል ኢርዶጋን።
ኢርዶጋን አክለው እንደተናገሩት እስራኤል በፍልስጤም እና ሊባኖስ የምታደርገውን ወረራ እንድታቆም ትራምፕ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ካስቆም ጥሩ ድምር ይሆናል።
ቱርክ እስራኤል በፍልስጤም እና በሊባኖስ ግዛቶች የምታካሂደውን ወረራ አጥብቃ የምታቀወም ሲሆን ከእስራኤል ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት አቋርጣለች። ቱርክ በእስራኤል ላይ በአለምአቀፉ የወንጀሎች ፍርድ ቤት የቀረበውን የዘር ማጥፋት ክስ ደግፋ ለመከራከርም ያመለከተች ሀገር ነች።
የትራምፕ ፕሬዝደንት መሆን በመካከለኛው ምስራቅ ባለው የኃይል ሚዛን ላይ ተጽዕኖ ይፈጥራል ያሉት ኢርዶጋን አሁን ያለውን የአሜሪካ ፖሊሲ መከተል በቀጣናው ያለውን ቀውስ እንደሚያባብሰው ገልጸዋል።
ቱርክ ከአሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በአዲስ መልክ እንዲስተካከል የሚፈልጉት ኢርዶጋን ከትራምፕ ጋር በስልክ ማውራታቸውን እና ቱርክን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። ኢርዶጋን አክለውም ትራምፕ ግብዣውን እንደሚቀበሉት ተስፋ አለኝ ብለዋል።