እስራኤል የዜጎቿን ህይወት ለመታደግ ወደ ኔዘርላንድ አውሮፕላኖች ልትልክ መሆኑን አስታወቀች
ጽ/ቤቱ እንደገለጸው ከሆነ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ነው
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳአር የደች መንግስት እስራኤላውያን በሰላም ወደ ኤየርፖርት እንዲደርሱ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
እስራኤል በደች ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ የእስራኤላውያን ህይወት ለመታደግ አውሮፕላን ልትልክ ነው።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በአምስተርዳም እስራኤላውያን ኢላማ ያደረገ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ሁለት የህይወት አድን አውሮፕላኖች እንዲላኩ ማዘዛቸውን ጽ/ቤታቸው በዛሬው እለት አስታውቋል።
ጽ/ቤቱ እንደገለጸው ከሆነ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ከእግር ኳስ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ነው።
የእስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስቴር በኔዘርላንድስ የሚገኙ እስራኤላውያን በሆቴላቸው እንዲቆዩ ማሳሰቡን ጽ/ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
የእስራኤል የደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤንግቪር በኤክሰ ገጻቸው "የእግርኳስ ጨዋታ ለማየት የሄዱ ደጋፊዎች የጸረ-ጽዮናዊ ተቃውሞ አጋጥሟቸዋል፤ አይሁድ እና እስራኤላውያን በመሆናቸው ብቻ ሊታሰብ በማይችል ጭካኔ ተጠቅተዋል" ብለዋል።
ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ከጨዋታው በኋላ የፍልስጤም ደጋፊዎች ከተማዋ በጆሃን ክሩይፍ ስቴዲየም ሰልፍ እንዳያደርጉ ብትከለክልም በእዚያ ሰልፍ ለማድረግ ሲሞክሩ 57 ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጿል።
ፖሊስ እስራኤላውያን ደጋፊዎች ከስታዲየም ጉዳት ሳይደርስባቸው መውጣታቸውን ቢገልጽም፣ ምሽት ላይ በከተማዋ ማዕከል ላይ በርካታ ግጭቶች መከሰታቸው ተዘግቧል።
የእስራኤል ጦር በዛሬው እለት እንደገለጸው አያክስ አምስተዳም ማካቢ ቴሌአቪቭን 5-0 ካሸነፈበት የእግርኳስ ጨዋታ በኋላ ከደች መንግስት ጋር በመተባበር የእስራኤላውያን ህይወት ለመታግ አውሮፕላን በፍጥነት ለመላክ እየተዘጋጀ ነው።
"ልኡኩ በእቃ ጫኝ አውሮፕላን የሚላክ ሲሆን የጤና እና የህይወት አድን ቡድንን ያካትታል" ብሏል ጦሩ።
በማህበራዊ የተለቀቁ ቪዲዮ ሰዎች በቡድን ሆነው በጎዳናዎች ሲሮጡ እና አንድ ሰው ሲደበደብ ያሳያል።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዲዮን ሳአር የደች መንግስት እስራኤላውያን በሰላም ወደ ኤየርፖርት እንዲደርሱ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።