ኢኮኖሚ
በህዳር 11 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር ስንት ብር ገባ?
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል
የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 122 ብር ገዝተው እስከ 125 ብር እየሸጡ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ተመን አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ በዛሬ ህዳር 11 2017 ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ ያቀረበ ሲሆን፤ አንድ ዶላርን በ122.8506 ብር እየገዛ በ125.3076 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ብርሃን ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.8509 ብር እየገዛ በ125.3079 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ጠቁሟል።
ንብ ባንክ ከሰሞኑ ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል፤ በዚህም አንድ ዶላርን በ120.4610 ብር እየገዛ በ122.8702 ብር እየሸጠ ነው።