ኢኮኖሚ
በህዳር 9 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች ባወጡት እለታዊ ተመን አንድ ዶላርን ከ120 እስከ 122 ብር እየገዙ ነው
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ20 ቀናት በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ ከ18 ቀናት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ዳሽን ባንክ እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ ዶላርን በ122.8506 ብር እየገዛ በ125.3076 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ እለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ላይ ማሻሻያ አድርጓል። በዚህም ባንኩ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ ከ1 ብር በላይ ጭማር በማድረግ በ122.5840 ብር እየገዛ በ125.0357 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ብርሃን ባንክም የህዳር 9 የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ ከ1 ብር በላይ ጨምሯል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ122.7905 ብር እየገዛ በ125.2463 ብር እየሸጠ ነው።