የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር መስመር አክሲዮን ማህበር የካርጎ ትራንስፖርት አገልግሎቱን በጸጥታ ስጋት ምክንያት ማቋረጡን ገልጿል
አክስዮን ማህበሩ ከሁለት ቀን በፊት አንስቶ አገልግሎት ማቆሙን ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈገ የድርጅቱ ኃላፊው ለአል ዐይን አማርኛ አረጋግጧል፡፡
በኢትዮጵያና በጂቡቲ መንግስት የተቋቋው የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር አክሲዮን ማህበር በጸጥታ ስጋት ምክንያት የካርጎ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ማቆሙን አስታውቋል፡፡ ኃላፊው አለ ያሉት የጸጥታ ስጋት ምን እንደሆነ ግልጽ አላደረጉም፡፡
ይሁን ማህበሩ አገልግሎት ለማቋረጥ ያስገደደው የጸጥታ ስጋት፤በአፋር እና ሶማሊ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈጠረው የሰሞኑ ግጭት ይሁን ወይም የፌደራል መንግስት ከህወሀት ጋር እያደረገው ያለው ጦርነት መሆኑን ኃላፊው ግልጽ አላደረጉም፡፡
ኃላፊው በሚቀጥለው ሳምንት የባቡር አገልግሎቱን መልሶ ለመጀመር እቅድ እንዳለው ለአልአይን አማርኛ ተናግረዋል፡
በኢትዮ-ጂቡቲ መስመር በሚገኝበት የሶማሊያና አፋር ክልል ሶሞኑን ግጭት መቀስቀሱንና ንፁሃም መሞታቸውን የሶማሌ ክልል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ በሁለቱ ክልሎች መካከል ተፈጥሯል ስለተባለው ግጭት የአፋር ክልል እስካሁን ያወጣው መግለጫ የለም፡፡