ኢትዮጵያን በቶኪዮ ኦሎምፒክ የሚወክሉ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ታዋቂ አትሌቶች እነማን ናቸው?
ኢትዮጰያ በአትሌቲክስ፣ በብስክሌት፣ በውኃ ዋና እና በቴኳንዶ ውድድሮች ትሳተፋለች
በቶኪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በ4 አይነት ስፖርታዊ ውድድሮ ች እንደምትሳተፍ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል
ኢትዮጵያ በጃፓን አስተናጋጅነት በሚካሄው የ”ቶኪዮ ኦሎምፒክ2020” ከ60 በላይ በሆኑ አትሌቶች እንደምትወከል የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
በነገው እለት በሚጀመረው 32ኛው ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ በ4 አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች ትሳተፋለች፡፡በአትሌቲክስ፣ በብስክሌት፣ በውኃ ዋና እና በቴኳንዶ ውድድሮች እንደምትካፈው ኮሜቴው አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን ወክለው ከሚወዳደሩ አትሌቶች መካከል አትሌት ለተሰንበት ግደይ፤ አትሌት ሹራ ቂጣታ፤ አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ታዋቂ አትሌቶች ናቸው፤ሜዳሊያ ያመጣሉ ተብሎ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡
አትሌት ለተሰንበት ግደይ
አትሌት ለተሰንበት ግደይ ኢትዮጵያን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ከሚወክሉ 65 ስፖርተኞች መካከል አንዷ ነች፡፡
አትሌቷ ሀገሯን በ10 ሺ ሜትር የምትወክል ሲሆን ለሜዳሊያ ግምት ከሚሰጣቸው አትሌቶችም ተጠቃሽ ነች፡፡ ለተሰንበት በፈረንጆቹ 2019 በኳታር ዶሃ በተካሄደው የ10ሺ ሜትር ውድድር የብር ሜዳሊያ ማሸነፏ ይታወሳል፡፡
አትሌት ለተሰንበት በሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ለ12 አመታት ተይዞ የነበረውን የ5ሺ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን በስፔን ማሻሻሏ ይታወሳል፡፡
አትሌት ለተሰንበት የ5ሺ ሜትርን ለማጠናቀቀ 14 ደቂቃ ከስድስት ሰከንድ ከ62 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶባት ነበር፡፡ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በቤጂንግ 14 ደቂቃ 11ሰከንድ ከ15 ማይክሮ ሰከንድ ነበር ያጠናቀቀችው፡፡
አትሌት ለተሰንበት በፈረንጆቹ በ2015 እና በ2017 ከ20 አመት በታች የዓለም አቀፍ ውድድር ማሸነፍ ችላ ነበር፡፡
ለተሰንበት ግደይ፤ በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እና ለኔዘርላንድ በምትሮጠው ሲፋን ሃሰን ተሻሽሎ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ክብረ ወሰንንም አሻሽላለች፡፡
አትሌት ሰለሞን ባረጋ
ሰለሞን ባረጋ በቶኪዮ ኦሊምፒክ በ 10ሺህ ሜትር የሚወዳደር ሲሆን በ 5 ሺ ደግሞ ተጠባባቂ ነው፡፡
ሰለሞን፤በፈረንጆቹ በ2016 በዓለም ከ 20 ዓመት በታች በፖላንድ ባይድጎስዝ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ5ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን በ 2017 በአፍሪካ ከ 20 የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በአልጄርያ ትሌምቼን በ5ሺ ሜትርም የወርቅ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል፡፡
በተመሳሳይ በ 2017 በሁለት ውድድሮች ላይ አሸናፊ ሲሆን በ 2018 ም በአትሌቲክስ ሻምፒዮናና በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዲሁም በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፎ ነበር፡፡
ሰለሞን በ2018 በዳይመንንድ ሊግ በ5ሺ ሜትር አሸናፊ ሲሆን 12 ደቂቃ ከ 43 ሰከንድ ከሁለት ማይክሮ በሆነ ሰዓት ገብቶ ነበር፡፡ ሰለሞን በ2021 በኔዘርላንድስ ሄንግሎ በተወዳደረበት ወቅት 10 ሺ ሜትሩን በ26 ደቂቃ ከ 49 ሰከንድ ከ46 ማይክሮ ሰከንድ ገብቷል፡፡
አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ
ዮሚፍ ቀጀልቻ በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ10ሜትር ኢትዮጵያን ወክሎ ይወዳደራል፡፡
ዮሚፍ ቀጀልቻ በ3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ የሚታወቅ ሲሆን በአንደኝነት ያጠናቀቀባቸው ብዙ ውድድሮች አሉ
በቅርቡ በኖርዌ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድርን አሸንፋል፤በውድድሩ ከዚህ በፊት በሃይሌ ገ/ስላሴ ተይዞ የነበረውን ክበረወሰን አሻሽሏል፡፡
ዩሚፍ አሁን ኢትዮጵያን በወከለበት 1000ሜትር የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ2ኛነት አጠናቋል፡
ዮሚፍ በፈረንጆቹ 2016ና 18 በአሜሪካና በዩናይትድ ኪንግደም የተካሄደውን የ3000 ሜትር ውድድር አሸንፋል፡፡
አትሌት ሹራ ቂጣታ
የለንደን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ሹራ ቂጣታ ኢትዮጵያን በማራቶን ይወክላል፡፡
ከውድድሩ በፊት የለንደን ማራቶንን ያሸንፋል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው የርቀቱ የክብረ ወሰን ባለቤት ኬኒያዊው ኤሊዩድ ኪፕቼጌ ነበር። በውድድሩ የተጠበቀው ሳይሆን ቀርቶ ኪፕቼጎ 8ኛ፤ ሹራ ደግሞ 1ኛ በመሆን አሽንፎ ነበር
አትሌት ሹራ ቂጣታ የለንደን ማራቶንን ያሸነፈው፤ በአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምክር መሆኑን መግለጹ ይታወሳል። መስከረም 26 ቀን ለተደረገው የለንደን ማራቶን ሹራ እና ቀነኒሳ አብረው ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ቀነኒሳ ግን እግሩ ላይ ባጋጠመው ጉዳት በውድድሩ ሳይሳተፍ መቅረቱን ይታወሳል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝና የቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020
ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ሊካሄድ የነበረው ቶኮዮ ኦሎምፒክ 2020 በአለም ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ወረርሸኝ ምክንያት መራዘሙ ይታወሳል፡፡በወረርሽኑ ምክንያት የተራዘመው ቶኪዮ ኦሎምፒክ2020 በነገው እለት ይጀመራል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት በኦሎምፒክ ውድድር ምክንያት ዳግም የኮሮና ወረርሽኝ ሊከሰት ይችላል ሲል ስጋቱን ገልጿል፡፡ የድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ወረርሽኝ “ዓለም የከሸፈበት ፈተና ነው” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን በውድድሩ ምክንያትከ100 ሺ በላይ ሰዎች በኮሮና ሊሞቱ ይችላሉ ብለዋል፡፡