ኢትዮ ቴሌኮም ይፋ ያደረገው የዲጂታል ፋይናንስ ገበያና የዲጂታል አክሲዮን ግዢና ሽያጭ ምንድን ነው?
ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው እለት ሁለት የፋይናነስ አገለግሎቶችን በይፋ አስጀምሯል
አገልግሎቶቹ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን በቴሌብር ለደንበኞቻቸው ለማቅረብ የሚያስችል ነው
ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው እለት ሁለት የፋይናነስ አገለግሎቶችን በይፋ ማስጀመሩን አስታውቋል።
በዛሬው እለት ይፋ የተደረጉት የፋይናነስ አገልግሎቶች የዲጂታል ፋይናንስ ገበያና የዲጂታል አክሲዮን ግዢና ሽያጭ መሆናቸውን ኩባያው አስታውቋል።
የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ገበያ፤ የፋይናንስ ተቋማት የማይክሮ ፋይናንስ ማለትም የብድር፣ ቁጠባ እና ኢንሹራንስ አገልግሎቶቻቸውን ለደንበኞቻቸው በአንድ ስፍራ በዲጂታል አማራጭ እንዲያቀርቡ የሚያስችል መሆኑን ኩባያው አስተውቋል።
- ኢትዮ ቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት 90 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቀደ
- ኢትዮ ቴሌኮም በአንድ ዓመት ውስጥ 13 ሚሊዮን አዲስ ደንበኞች ለማፍራት ማቀዱን ገለጸ
በዚህም ደንበኞች ካሉበት ሆነው የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተባለ ሲሆን፤ አገልግሎቱ የደንበኞችን የብድር እንቅስቃሴ እና በወቅቱ የመመለስ ልምድን በማገናዘብ እና የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በሚሰራ የብድር ቀመር መሰረት የሚከናወን በመሆኑ ያለምንም የንብረት መያዣ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ነው።
የዲጂታል ፋይናንስ ገበያ ባንኮች ምንም አይነት የካፒታል ኢንቨስትመንት ማድረግ ሳይጠበቅባቸው ኢትዮ ቴሌኮም በገነባው ፕላትፎርም ተጠቅመው የፋይናንስ አገልግሎቶቻቸውን ከ40 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ የቴሌብር ደንበኞች በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ የሚችሉበትም ነው።
ኢትዮ ቴልኮም ሌላ ይፋ ያደረገው አገልግሎት የዲጂታል አክሲዮን የግዢና መሸጫ ሲሆን፣ ይህም ፍቃድ የተሰጣቸው የቢዝነስ ተቋማት የአክሲዮን ግዢና ሽያጭ ሂደታቸውን ዲጂታል በማድረግ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ የሚያከናውኑበትና አክሲዮናቸውን ለማህበረሰቡ ተደራሽ የሚያደርጉበትን ነው።
የፋይናንስ ተቋማት ወጪ ቆጣቢ የሆነው የዲጂታል አክሲዮን ግዢና ሽያጭ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ጋብዟል።