ኢኮኖሚ
ኢትዮ ቴሌኮም በአንድ ዓመት ውስጥ 13 ሚሊዮን አዲስ ደንበኞች ለማፍራት ማቀዱን ገለጸ
ድርጅቱ በ2016 በጀት ዓመት 90 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅጃሉሁም ብሏል
በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ አንድ ሺህ ገደማ የሞባይል ኔትወርክ ጣቢያ እንደሚገነባ ገልጿል
ኢትዮ ቴሌኮም በአንድ ዓመት ውስጥ 13 ሚሊዮን አዲስ ደንበኞች ለማፍራት ማቀዱን ገለጸ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን የ2016 በጀት ዓመት እቅድን ይፋ አድርገዋል።
ስራ አስፈጻሚዋ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በተያዘው በጀት ዓመት ከአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎቶች 90 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል ብለዋል።
ድርጅቱ በ2016 በጀት ዓመት 13 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት የተቋሙን አጠቃላይ ደንበኞች ቁጥር ወደ 92 ሚሊዮን የማድረስ ውጥን መያዙንም ሀላፊዋ አክለዋል።
የቴሌብር ደንበኞችን ወደ 44 ነጥብ 1 ሚሊዮን፣ የሞባይል ድምጽ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 75 ሚሊዮን እንዲሁን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን ወደ 41 ሚሊዮን ማድረስም የተቋሙ ሌላኛው ግብ ነው ተብሏል።