ኢኮኖሚ
የኢትዮ ቴሌኮም በ2015 ዓ.ም ያስመዘገባቸው ስኬቶችን የትኞቹ ናቸው?
ድርጅቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 76 ቢሊዮን ብር ገደማ አጠቃላይ ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል
የኢትዮ ቴሌኮም ጠቅላላ ደንበኞችም ወደ 72 ሚሊዮን ከፍ ማለቱ ተገልጿል
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በታሪክ ትልቁን ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል።
የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የተቋሙን ዓመታዊ አፈጻጸም አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
ከተገኘው አጠቃላይ የ76 ቢሊዮን ብር ውስጥ አብዛኛው ገቢ የተገኘው ከድምጽ ጥቅል እና ኢንተርኔት አገልግሎት እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ምንዛሬ አገልግሎቶች 164 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ ወደ አገልግሎት ያስገባው ቴሌብር 680 ቢሊዮን ብር የገንዘብ ዝውውር የተፈጸመበት ሲሆን የደንበኞቹ ብዛትም 34 ሚሊዮን መድረሱ ተገልጿል።