ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የፈረመችውን የወደብ ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ተበላሽቷል
ሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች ድንበሬን ጥሰዋል ስትል ከሰሰች።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሶማሊያ አምባሳደር የኢትዮጵያ ወታደሮች የሶማሊያን ድንበር ጥሰው በመግባት ከአካባቢው የጸጥታ ኃይል ጋር ፍጥጫ እንዲፈጠር አድርገዋል ሲሉ ከሰዋል።
ቢያንስ 3000 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልእኮ(ኤቲኤምአይኤስ) ስር ሆነው በሶማሊያ ውስጥ ተሰማርተው ሰፊውን የሶማሊያ ክፍያ የያዙትን አልሸባብን እና እስላማዊ ታጣቂዎችን እየተዋጉ ይገኛሉ።
ሌሎች ከ5000-7000 የሚሆኑ የኢትዮጵያ ወታደሮች ደግሞ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ስምምነት በተለየዩ ግዛት ሰፍረው እንደሚኙም ተዘግቧል።
- ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችውን ስምምነት ውድቅ ካላደረገች መነጋገር እንደማትፈልግ ሶማሊያ ገለጸች
- ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር ከሀገሯ ማባረሯን ገለጸች
የኢትዮጵያ ወታደሮች ባለፈው ቅዳሜ እለት ከአልሸባብ የሚቃጣውን ጥቃት ለመቃኘት በሶማሊያዋ ሂራን ግዛት ገብተው አሁድ እለት መውጣታቸውን ሮይተርስ የአይን እማኞችን ጠቅሶ ዘግቧል።
በሮይተርስ በዘህ ዘገባው ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምላሽ አለማግኘቱን ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መንግስት በዚህ ክስ ጉዳይ እስከአሁን ያለው ነገር የለም።
በተመድ የሶማሊያ አምባሳደር አቡካር ዳሂር ኦስማን የኢትጵያ ወታደሮች ድንበር በመጣሳቸው ምክንያት ሶማሊያ የኤቲኤምአይኤስ ወታደሮችን ማስወጫ ጊዜ ከሐምሌ ወደ መስከረም እንድታራዝም አስገድዷታል ብለዋል።
የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ተልእኮው ባለፈው ታህሳስ ወር ነበር ለመውጣት የተስማማው።
የሰላም አስከባሪዎች እንዲወጡ የሚፈለገው የሶማሊያ መንግስት ከአልሸባብ ሊቃጣ የሚችለውን ጥቃት መመከት እንደሚችል እየገለጸ ነው።
በሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ ኢትዮጵያ ሶማሊያ የራሷ ግዛት አድርጋ ከምታያት ሶማሊላንድ ጋር ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ የወደብ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ ነው።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ለንግድ እና ለባህር ኃይል ሰፈር የሚሆን 20 ኪሎሜትር የባህር ጠረፍ ቦታ እንድታገኝ እና በምትኩ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድሰጥ ያስችላል ተብሎ ነበር።
ሶማሊያ ይህ ስምምነት የሶማሊያን ሉአላዊት የሚጥስ ነው ስትል በጽኑ ተቃውማዋለች። ከዚህ በተጨመሪም ሶማሊያ የኢትዮጵያን አምባሳደር በማባረር ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱን ከፍ እንዲል አድርጋዋለች።
ኢትዮጵያ በአንጻሩ ስምምነቱ የሚጥሰው እምነትም ሆነ ህግ የለም የሚል መልስ መስጠቷ ይታወሳል።
በስምምነቱ "የተጣሰ ሕግና የተሰበረ እምነትም የለም"- የኢትዮጵያ መንግስት
ሶማሊያ ግን ኢትዮጵያ ስምምነቱን ከልሰረዘች ለመነጋገር ዝግጁ አለመሆኗን ገልጻልች።