የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 7 ነጥብ 5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ 1ኛ እንዲሁም ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ደግሞ 3ኛ ነው ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ የሀገሪቱ ሀብት በአጠቃላይ 6.16 ትርሊዮን ብር ደርሷል ብለዋል
ዘንድሮው በጀት ከመት በማክሮ ኢኮኖሚው የ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገለጹ፡፡
ጠቅለላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ነው፡፡
ዓለም በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትና የተለያዩ ፈተናዎች ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ቢያጋጥመውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በቀላሉ የማይሰበር መሆኑ ታይቷል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስተሩ፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ 1ኛ እንዲሁም ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ደግሞ 3ኛ መሆኑም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ባንክን መረጃ ዋቢ በማድረግ የገለጹት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተሩ የዓለም ባንክ መረጃን ተንተርሰው ባቀረቡት ማብራሪያም፣ የሀገሪቱ ሀብት በአጠቃላይ 6.16 ትርሊዮን ብር መድረሱን ገልጸው፣ የነፍስ ወከፍ ገቢ ደግሞ 1 ሺህ 112 ዶላር ደርሷል ብለዋል።
የባለፈው አመት አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገት 6.4 ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተመዘገበው እድገት የግብርና (6.1 በመቶ ድርሻ)፣ ኢንዱስትሪ (4.9 በመቶ) እንዲሁም የአገልግሎት (7.6 በመቶ ድርሻ) ዘርፎች ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው አንስተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘንድሮ በማክሮ ኢኮኖሚው ከባለፈው አመት በተሻለ የ7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት ይጠበቃልም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዓለም ሁሉ ፈተና ነው ስላት የዋጋ ግሽበት በተመለከተ ከፓርላማ አባላት ለተነሳለቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያም፤ የአቅርቦትና ፍለጎት አለመጣጣምና የገበያ ትስስር አለመኖሩ ለዋጋ ግሽበት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ይሁን እንጅ ባለፉት አራት ወራት በተወሰዱ የዋጋ ማረጋጋት ስራዎች የዋጋ ግሽበት በመቀነስ ሂደት ላይ መሆኑ ተናግረዋል፡፡
በተለይም መንግስት የአቅርቦት እጥረት ባለባቸው ግብአቶች ቀጥተኛ ድጋፍ በማድረጉ፣ አርሶ አደሩ በቀጥታ ምርቱን የሚያቀርብባቸው የእሁድ ገበያዎች መስፋፋት እየተለመደ መምጣቱ የዋጋ ግሽበቱ እየቀነሰ ለመምጣቱ በምክንያትነት ጠቅሰዋል።
9.5 ሚሊዮን ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ በመንግስት የምገባ መርሃ-ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውም ችግሩ እየቀነሰ እንዲመጣ አስተዋጽኦ ማድረጉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በተለያዩ የምገባ ማዕከላት 30 ሺህ ሰዎች የሚያገኙት የምገባ አገልግሎትም ለዋጋ መረጋጋቱ አስተዋጽኦው ቀላል አለመሆኑን አመልክተዋል።
የገቢያ ትስስሩን በማስፋፋት አቅርቦትን በማሳደግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑንም አክለዋል፡፡
ብክነትን በመቀነስ፣ በሁሉም ቦታ ላይ ማርታማነትን ማሳደግ፣ ከሌብነት እና ከስንፍና በመታቀብ፣ በጎ ነገሮችን እየመረጡ በመጠቀም የዋጋ ግሽበትን በዘላቂነት መቋቋም እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስተሩ በቅርቡ ስለተከለከሉ የሸቀጥ አይነቶችን በተመለከተ ሲናገሩም ካለው የኢኮኖሚ ጫና አንጻር የተወሰደው እርምጃ ተገቢ እንደነበር አነስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከውጭ ለምታስገባቸው 6ሺህ ሸቀጣሸቀጦች ከ18 ቢሊዮን ዶላር በላይ በዓመት ለኢምፖርት ታወታለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የታገዱት ሸቀጣሸቀጦች 38 ብቻ መሆናቸው አስገንዝቧል፡፡
የሸቀጣሸቀጦቹ መታገድ አላስፈላጊ የውጭ ምንዛሪ ከማስቀረት እና ለሀገር ውስጥ ምርቶችን አድል ከመስጠት አንጻር ፋይዳ እንዳለውም ተናግራል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡