በጦርነቱ ምክያት የዩክሬን ኢኮኖሚ በ40 በመቶ እንደሚቀንስ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስቴር ገለጸ
ሩሲያ የህልውና አደጋ ከተደቀነባት ኑክለር ልትጠቀም እንደምትችል ማስወታቋ ይታወሳል
ሩሲያ ወደ ግጭት የገባቸው የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ ሶቬት አባል ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደሚያሰጋት በመግለጽ ነበር
ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፈተችው “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” ምክንያት በዚህ ሩብ አመት 16 በመቶ የቀነሰ ሲሆን በፈረንጆቹ 2022 ደግሞ በ40 በመቶ እንደሚቀንስ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው በርቀት መስራት ያልተቻለባቸው ቦታዎች ይበልጥ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ላይ “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” መክፈቷን ተከትሎ በሩሲያ እና በአውሮፓ እና አሜሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ ገብቷል፡፡
በምእራባውያን ተጽእኖ አማካኝነት የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ፤አብዛኞቹ ሀገራት የሩሲያን ወታደራዊ ዘመቻ አውግዘዋል፤ የተወሰኑ ሀገራት ሩሲያን እንደማያወግዙ ጠቅሰው የተቃወሙም ነበሩ፡፡
ምእራባውያን ሀገራት ሩሲያን እንዲያወግዙ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፤ ፕሬዝዳንት ፑቲን ስልጣን ላይ መቆየት የለባቸው የሚል ንግግር አስምተው ነው ነበር፡፡ ሩሲያ በፕሬዝዳንቱ አስተያየት ቁጣዋን መግለጻ ይታወሳል፡፡
ሩሲያ ወደ ግጭት የገባቸውም የኔቶ ጦር ዩክሬንን ጨምሮ ወደ ቀድሞ ሶቬት አባል ሀገራት እየተስፋፋ ነው ይህም ለደህንነቴ ያሰጋኛል በሚል ነበር፡፡ ሩሲያ እና ዩክሬን ወደ ግጭት ውስጥ ከገቡ በኋላ ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉንም አይነት ማእቀብ ጥለዋል፤እየጣሉም ነው፡፡
የሩሲያ መንግስት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፓስኮቭ ከአሜሪካው ፒቢኤስ ጋር በደረጉት ቆይታ ሩሲያ ህልውናዋን አደጋ ውስጥ የሚከት ስጋት ካጋጠማት ብቻ የኑክለር ጦር መሳሪያ ልትጠቀም እንደምትችል ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ስለ ፑቲን ስልጣን መቆየት የሰጡት አስተያየት የሚረብሽ እና ግለሰብ ላይ ያነጣጠረ ስድብ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ ኔቶ የመፋጠጫ ማሽን ነው ብለዋል፡፡
“በዩክሬን ውስጥ በምናደርገው ዘመቻ የኑክለር ጦር መሳሪያ የምንጠቀምበት ምክንያት የለም፣…እኛ ባለን ግልጽ ፖሊሲ ላይ እንደተቀመጠው የኑክለር ጦር መሳሪያ የምንጠቀም እንደሀገር መቀጠላችን አደጋ ከተጋረጠት ብቻ ነው፣ ስጋቱን ለማጥፋት ኑክለር እንጠቀማን” ብለዋል፡፡
ሩሲያ እና ዩክሬን ችግሩን ለመፍታት በቱርክ አመቻችነት እየተደራደሩ ነው፡፡