ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ አገኘች
የዓለም ባንክ እና ኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል
የዓለም ባንክ ገንዘብ የኤሌክትሪክ ሀይል መሰረተ ልማት ዝርጋታን ጨምሮ ለምግብ ዋስትና እና ሌሎች ስራዎች የሚውል ነው ተብሏል
ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ከ850 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ አገኘች፡፡
ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ97 ቢሊዮን ብር እርዳታ እና ብድር ስምምነት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተወካይ የሆኑት ኦስማን ዲዮን ተፈራርመዋል ተብሏል፡፡
ከዓለም ባንክ ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ 850 ሚሊዮን ዶላር ያህሉ በእርዳታ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡
ቀሪው ገንዘብ ደግሞ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት እና ለማከናወን በሚል በብድር መልኩ ከባንኩ እንደተሰጠ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡
በእርዳታ ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ለገጠር አካባቢዎች የምግብ ዋስትና፣ የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎችን ለመደገፍ፣ 82 ዶላሩ ደግሞ በከተማ አካባቢዎች ምግብ ዋስትና ስራዎችን ለማረጋገጥ ይውላል ተብሏል፡፡
በአዲስ አበባ ለ15 ቀናት የተደረገው የአይ ኤም ኤፍ እና ኢትዮጵያ ውይይት በምን ተቋጨ?
እንዲሁም 340 ሚሊዮን ዶላሩ በቆላማ አካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እና የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡
ቀሪው 275 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ በከተሞች አካባቢ ያሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት እንደሚውልም ተገልጿል፡፡
የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች ቡድን በአዲስ አበባ ለሁለት ሳምንታት ከኢትዮጵያ በለስልጣናት ጋር ሲመክር ቆይቶ መመለሱ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት ወደ አዲ አበባ የመጣው የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች ቡድን ስኬታማ ቆይታ አድርጎ መመለሱን የገለጸ ሲሆን ያልተስማሙባቸው ጉዳዮች እንዳሉ እና ተጨማሪ ውይይቶች በቀጣይ እንደሚደረጉም አስታውቋል፡፡