በጥቅምት 26 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ120 እስከ 121 ብር መግዣ፤ እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 26 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ እለታዊ የምንዛሬ ተመኑ ላይ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ማሻሻያ ባያደርገውም ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክ የጥቅምት 26 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ120.4570 ብር እየገዛ በ122.8661 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
አዋሽ ባንክም የጥቅምት 26 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ120.0062 ብር እየገዛ በ122.4063 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ንብ ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2683 ብር ገዝቶ በ121.6537 ብር እየሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ ምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።