በጥቅምት 21 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?
የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ118 እስከ 121 ብር መግዣ፤ ከ119 እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላር በ119 ብር ገዝቶ በ121 ብር እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 21 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክ የጥቅምት 21 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ120.0064 ብር እየገዛ በ122.4065 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
ንብ ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ118.3217 ብር ገዝቶ በ120.6882 ብር እየሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ ምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
.