በጥቅምት 23 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ገባ?
የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ120 እስከ 121 ብር መግዣ፤ እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 23 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል።
በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ዛሬም ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ የጥቅምት 23 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክም የጥቅምት 23 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ120.0064 ብር እየገዛ በ122.4065 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
አዋሽ ባንክም የጥቅምት 23 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ120.0062 ብር እየገዛ በ122.4063 ብር እየሸጠ ይገኛል።
አቢሲኒያ ባንክም የጥቅምት 23 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ120.0068 ብር እየገዛ በ122.4069ብር እየሸጠ ይገኛል።