በጥቅምት 22 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?
የግል ንግድ ባንኮች ለ1 ዶላር ከ120 እስከ 121 ብር መግዣ፤ እስከ 123 ብር መሸጫ ዋጋ አውጥተዋል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ119 ብር እየገዛ፤ በ121 ብር እሸጠ ይገኛል
ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መግዣና መሸጫ መሃል ያለው ልዩነት እንዲቀራረብ ባሳሰበ ማግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ላይ ለውጥ ታይቷል።
ባንኮች በውጭ ምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸው ላይ ካደረጉት ቅናሽ ባሻገር በመግዣ ዋጋቸውም ላይ ከ10 ብር በላይ ጭማሪ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 22 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል።
በዚህምአንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2044 ብር እየገዛ ሲሆን፤ በ121.5885 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኦሮሚያ ባንክ ዛሬም ከፍተኛውን የዶላር መግዣ ዋጋ አቅርቧል። ባንኩ የጥቅምት 22 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የሰሞኑን ዋጋ አስቀጥሎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ121.3066 ብር እየገዛ በ123.7327 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ዳሽን ባንክም ከፍተኛ የምንዛሬ ዋጋ ካቀረቡት ውስጥ ሲሆን፤ ዳሽን ባንክ የጥቅምት 22 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ የትናንቱን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ120.0064 ብር እየገዛ በ122.4065 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።
አንበሳ ባንክም የጥቅምት 22 2017 ዓ.ም እለታዊ የምንዛሬ ተመኑም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ120.0892 ብር እየገዛ በ122.4910 ብር እየሸጠ ይገኛል።
ንብ ባንክ ደግሞ ከትናንተናው ዋጋው መጠነኛ ጭማሪ ያደረገ ሲሆን፤ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ119.2683 ብር ገዝቶ በ121.6882 ብር እየሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ ምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።