የኢትዮጵያ መንግስት ምዕራባውያን በፕሬስ ነጻነት አያያዝ ዙሪያ ያቀረቡበትን ትችት እንደማይቀበለው ገለጸ
በአዲስ አበባ የሚገኙ ምዕራባውያን ሀገራት ኢምቢሲዎች የኢትዮጵያን የጋዜጠኞች አያያዝ ተችተዋል
የዓለም የፕሬስ ቀን ዛሬ በመላው ዓለም ተከብሯል
የኢትዮጵያ መንግስት ምዕራባውያን በፕሬስ ነጻነት አያያዝ ዙሪያ ያቀረቡበትን ትችት እንደማይቀበለው ገለጸ
በአዲስ አበባ የሚገኙ ምዕራባውያን ሀገራት ኢምቢሲዎች 'የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን' አስመልክተው ባወጡት የጋራ መግለጫ የኢትዮጵያን የጋዜጠኞች አያያዝ ተችተዋል።
ሀገራቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው "ማስፈራሪያ እና አግባብነት የሌለው እስር ይደርሰባቸዋል" ብለዋል።
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ሀገራቱ በኢምባሲዎቻቸው በኩል ያወጡትን መግለጫ እንደማይቀበለው ገልጿል።
ኢትዮጵያ ከሁሉም አጋሮቿ እና ባለድርሻ አካላት ጋር ገንቢ የሆነ ንግግር ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን የገለጸው ሚኒስቴሩ "አባታዊ ወደሆነ መግለጫ ማምራት የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚጎዳ እና የህግ የበላይነት የሚሸረሽር" ነው ብሏል።
ኢምባሲዎቹ ካሉበት ሀገር በእንዲህ አይነት መልኩ ግንኙነት ማካሄድ ተገቢነት የለውም ሲል ገልጿል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሲፒጄ እና ሂማን ራይትስ ዎችን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለአግባብ የታሰሩ ጋዜጠኞች መኖራቸውን በመግለጽ ባለስጣናት እንዲለቋቸው በተለያየ ጊዜ ጠይቀዋል።
የጋዜጠኞቾ መብት ተሟጋች የሆነው ሲፒጄ ከወራት በፊት ባወጣው አመታዋ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ ስምንት ጋዜጠኞችን በማሰር ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ውስጥ ሁለተኛ የጋዜጠኞች አሳሪ አድርጓታል።