አይኤምኤፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያሉት ልዩነቶች እስካሁን አለመፈታታቸውን ገለጸ
ኢትዮጵያ በብዙ አመታት ውስጥ ባለፈው ታህሳስ ወር ብድር መክፈል ካልቻሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ መካተቷ ተዘግቦ ነበር
ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ብድር ለማግኘት ገንዘቧን ማዳከም ሊጠበቅባት ይችላል
አይኤምኤፍ በብድር ጉዳይ ከኢትዮጵያ ጋር ያሉት ልዩነቶች እስካሁን አለመፈታታቸውን ገለጸ።
በብድር እና በማሻሻያ ፕሮግራም ዙሪያ በዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ ) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያሉት ልዩነቶች እስካሁን አልተፈቱም፤ ነገርግን ንግግሮች ይቀጥላሉ ሲሉ አንድ ከፍተኛ አይኤምኤፍ ባለስልጣን ባለፈው አርብ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ብድር ለማግኘት በጥቁር ገበያ ከመደበኛው ምንዛሬ ዋጋ ከ50 በመቶ በታች ባነሰ ዋጋ በዶላር የሚመነዘረውን ገንዘቧን ማዳከም ሊጠበቅባት ይችላል።
ተቋሙ ይህን በቅደመ ሁኔታነት ማስቀመጡን ባያረጋግጥም፣ ብዙ ጊዜ በገበያ የሚወሰን የምንዛሬ ተመን እንዲኖር ይፈልጋል።
ኢትዮጵያ በብዙ አመታት ውስጥ ባለፈው ታህሳስ ወር ብድር መክፈል ካልቻሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ መካተቷ ተዘግቦ ነበር።
አይኤምኤፍ እና የአለም ባንክ በዋሽንግተን ባካሄዱት ስብሰባ የአይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ልኡክ ኃላፊ አልቫሮ ፕሪስ ቻቫሪ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር የሚደረጉት "ድርድሮች እንደቀጠሉ ናቸው" ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
"ልዩነቶች አሁንም አሉ፤ ይፈታሉ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ" ያሉት ኃላፊው አልተፈቱም ያሏቸው ልየነቶቹ ምን እንደሆኑ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።
ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2020 ወዲህ ከአይኤምኤፍ ብድር አላገኘችም።
በኢትዮጵያ የፋይናንስ ድጋፍ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት መደረሱን የገለጹት ፕርስ ቻቫሪ ከአይኤምኤፍ የ3.5 ቢሊዮን ዶላር ልታገኝ ነው በሚሉት ሪፖርቶች ላይ ግን አስተያየት ከመስጥ ተቅጥበዋል።
እንደዘገባው ከሆነ ኢትዮጵያ ከአለም ባንክም የ3.5 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት እየተነጋገረች መሆኑን እኝህ ዲፕሎማት ተናግረዋል።
በቅርቡ ኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የብሔራዊ ባንክ ገዥው ማሞ ምህረቱ ከአይኤምኤፍ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከአለም ባንክ ስራ አስፈጻሚዎች ጋር በዋሽንግተን መወያየታቸውን ሮይተርስ በዘገባው ጠቅሷል።