ኢትዮጵያ የጉበት በሽታ እየተስፋፋባቸው ካሉ የዓለም ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ
የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ በጉበት በሽታ የሚጠቁ ዜጎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ካለባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት ብሏል
በዓለም ላይ በየዕለቱ 3 ሺህ 500 ሰዎች በጉበት በሽታ እየሞቱ እንደሆነም ድርጅቱ አስታውቋል
ኢትዮጵያ የጉበት በሽታ እየተስፋፋባቸው ካሉ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ፡፡
የዓለም ጉበት በሽታ ጉባኤ በፖርቹጋል ተካሂዷል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ እንደተገለጸው በዓለማችን በየዕለቱ 3 ሺህ 500 ሰዎች በጉበት በሽታ እየሞቱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የኤችአይቪ፣ ሄፓ ታይተስ እና ተላላፊ በሽታዎች ፕሮግራም ሃላፊ ሜግ ዶሂርቴ እንዳሉት በጉበት በሽታ ከሚሞቱት ውስጥ 83 በመቶዎቹ በሄፓታይተስ ቢ በተሰኘው የጉበት በሽታ የሚሞቱ ናቸው ብለዋል፡፡
በጉበት በሽታ የሚጠቁ ዜጎች እየጨመረ ነው ያሉት ሃላፊው 63 በመቶ ያህሉ ተጠቂዎች በአፍሪካ የሚገኙ ዜጎች እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡
በየዕለቱ ስድስት ሺህ ሰዎች በጉበት በሽታ እየተጠቁ ነው ያለው የዓለም ጤና ድርጅት ተጠቂዎች በቂ ህክምና እያገኙ እንዳልሆነም የዓለም ጤና ድርጅት በድረገጹ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ስብ ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ በሰው ጤና ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች
በሽታው ከተስፋፋባቸው ሀገራት መካከል 75 በመቶ ያህሉ ሽታው እየተስፋፋባቸው ካሉ የዓለማችን ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ፣ቻይና፣ ባንግላዲሽ፣ ናይጀሪያ፣ሕንድ እና ኢንዶኔዢያ ተጠቅሰዋል፡፡
በ187 ሀገራት በተጠና ጥናት መሰረትም የጉበት በሽታ በየዓመቱ እየጨመረ እንደሆነም የተገለጸ ሲሆን ከጠቅላላው ተጠቂዎች ውስጥ መድሃኒት እያገኙ ያሉት ሶስት በመቶዎቹ ብቻ ናቸውም ብሏል፡፡
በአፍሪካ ከሚወለዱ አምስት ህጻናት መካከል አንዱ ብቻ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት እንደሚወስዱም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡