የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ ዘንድ የሚከበር በዓል ነው
የጥምቀት በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት ተከብሮ ውሏል።
በመላ ሀገሪቱ ትናንት ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ በመውረድ በዚያው ማደራቸው ይታወቃል።
ዛሬ ማለዳ በዓሉ ታቦታቱ ባደሩባቸው ጥምቀተ ባህር በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እና ስርዓት ጥምተው ተከብሮ ውሏል።
የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ በጽዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሯል።
ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ነው የተከበረው።
በዓሉ በጎንደር ከተማ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከብሯል።
በበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ላይ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲሁም የፌደራል እና የክልል መንግስታት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ አርቲስቶች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የደብር አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም በዓሉ በባህር ዳር፣ በሃዋሳ፣ በጅማ፣ በሻሸመኔ፣ በሆሳዕና፣ በባቱ፣ በደብረ ብርሃን፣ በነቀምቴ ፣በጋምቤላ ፣ በምንጃር ኢራንቡቲ እና በተለያዩ አካባቢዎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ ውሏል።
የጥምቀት በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በፈለገ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን ዕለት በማሰብ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር በዓል ነው።