የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደግሞ 1 ዶላር በ95 ዶላር እገዛ፤ በ101 እየሸጠ ይገኛል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ከካሳለፍነው ሳምን ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ እስከ 44 ብር የሚደርስ ጭማሪ ታይቷል።
ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የሀምሌ 29 2016 የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 7 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት በወጋገን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ101.6434 ብር እየተገዛ በ113.8406 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በዳሽን ባንክ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.9253 ብር እየተገዛ በ112.0271 ብር እየተሸጠ መሆኑን ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
በኦሮሚያ ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.8445 ብር እየተገዛ በ113.8445 ብር እየተሸጠ ይገኛል።
አዋሽ ባንክ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ100.1531 ብር እየተገዛ በ111.1699 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከግል ባንኮች ዝቅ ያለ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ አውጥቷል። ባንኩ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ95.6931 ብር እየገዛ በ101.4347 ብር እየሸጠ ነው።