በአዋሽ ባንክ 1 ዶላር በ76 ብር እየተገዛ በ77 እየተሸጠ ውሏል
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በዲሱን የምንዛሬ ተመን ከትናንት ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት መሸጋገሩን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ እስከ 19 ብር ጭማሪ ታይቷል።
ይህንን ተከትሎ ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 2 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ74.7364 ብር እየተገዛ በ76.2311 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዩሮ 80.8797 ብር እየተገዛ በ82.4973 ብር እየተሸጠ መዋሉን የባንኩ የዋጋ ዝርዝር አስታውቋል።
በአዋሽ ባንክ ደግሞ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ76.2351 ብር እየተገዛ በ77.7598 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
አንድ ዩሮ ደግሞ 82.6619 ብር እየተገዛ በ84.3151 ብር እየተሸጠ መዋሉን የባንኩ የዋጋ ዝርዝር አስታውቋል።
በሌሎች ባኮችም የውጨ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ላይ የሳንቲም ልዩነቶች መታየታቸውን መታዘብ ችለናል።