በበቡና ባንክ 1 ዶላር በ81 ብር እየተገዛ በ85 ብር እየተሸጠ ነው
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በዲሱን የምንዛሬ ተመን ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ እስከ 23 ብር ጭማሪ ታይቷል።
ይህንን ተከትሎ ባንኮች በማህራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት የውጭ ምንዛሬ ተመን ዝርዝር ላይ ከሳንቲሞች እስከ 3 ብር የሚደርስ የዋጋ ልዩነት ታይቶባቸዋል።
በዚህም መሰረት ወጋን ባንክ ዛሬ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን መሰረት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ83.4681 ብር እየተገዛ በ85.1374 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
እንዲሁም በወጋገን ባንክ አንድ ዩሮ 87.6115 ብር እየተገዛ በ89.3611 ብር እየተሸጠ መሆኑን የባንኩ የዋጋ ዝርዝር አስታውቋል።
በቡና ባንክ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ81.2206 ብር እየተገዛ በ85.73813058 ብር የተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
አንድ ዩሮ ደግሞ 87.0602 ብር እየተገዛ በ89.2651 ብር እየተሸጠ መሆኑን የባንኩ የዋጋ ዝርዝር አስታውቋል።
በኦሮሚያ ብህረት ስራ ባንክም አንድ የአሜሪካ ዶላር በ81.0389 ብር እየተገዛ በ84.2805 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
በዳሸን ባንክ ደግሞ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ80.9515 ብር እየተገዛ በ84.9994 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
በአዋሽ ባንክ በዛሬው እለት አንድ የአሜሪካ ዶላር በ79.9724 ብር እየተገዛ በ82.3716 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
በሌሎች ባኮችም የውጨ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ላይ የሳንቲም ልዩነቶች መታየታቸውን መታዘብ ችለናል።