ለነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ምክንያት በዓለም ገበያ ላይ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሆኑ ተነግሯል
የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ዛሬ ምሽት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫው ከዛሬ ሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ አይነቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መደረጉን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።
በዓለም ገበያ ላይ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሠረት በማድረግ መጠነኛ የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ ላይ የሚውለው የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ፤
ቤንዚን …………………………… ብር 82.60 በሊትር
ነጭ ናፍጣ……………………… ብር 83.74 በሊትር
ኬሮሲን ……………………………. ብር 83.74 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ………………… ብር 70.83 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ………………… ብር 65.48 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ…………………. ብር 64.22 በሊትር መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።