ከነዳጅ የኃይል ምንጭ ወደ ታዳሽ ኃይል መሸጋገር ያሉት ፈተናዎች
በታዳሽ ኃይል አጠቃቀም ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ውስንነት ሊያጋጥም ይችላል
በነዳጅ ላይ ጥገኛ የሆኑ ኢኮኖሚዎች በሚፈጠረው ሽግግር ኢኮኖሚያዊ አመረጋጋት ሊያጋጥማቸው ይችላል
ከነዳጅ የኃይል ምንጭ ወደ ታዳሽ ኃይል መሸጋገር ያሉት ፈተናዎች
ነዳጅን ከመጠቀም ወደ ታዳሽ ኃይል የመሸጋገር ሂደት በርካታ ፈተናዎች አሉት።
ሊያጋጥሙ የሚችሉት ዋናዋና ችግሮች የሚከተሉት ናቸው።
1) የመሰረተልማት ሽግግር
እንደ ሶላር፣ ንፋስ እና የውሃ ኃይል የመሳሰሉትን የታዳሽ ኃይል ምንጮች ለመጠቀም ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ መሻሻል ያስፈልጋል።
2) ወጥነት ያለመኖር
ነዳጅ በማንኛውም የአየር ሁኔታ አገልግሎት ይሰጣል። ነገርግን እንደ ሶላር እና ንፋስ ያሉት የታዳሽ ኃይል ምንጮች በአየር ንብረት ምክንያት የሚለዋወጡ ናቸው። አስተማማኝ የሆነ ክምችት ማዘጋጀት እና የአቅርቦት መዋዠቅን መቆጣጠር ወሳኝ ነው።
3) ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ
በነዳጅ ላይ ጥገኛ የሆኑ ኢኮኖሚዎች በሚፈጠረው ሽግግር ኢኮኖሚያዊ አመረጋጋት ሊያጋጥማቸው ይችላል። ከነዳጅ ጋር በተያያዙ ኢንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሰራተኞች ስራቸውን ያጣሉ።
4) ዋጋ
የታዳሽ ኃይል ወጭ አነስተኛ ቢሆንም ለማቋቋም ግን ከፍተኛ ገንዘብ ያስፈልጋል። ይህን ሽግግር መንግስታት እና የንግድ ተቋማት ሊደጉሙት ይገባል።
5) የጂኦፖለቲካል ፈተናዎች
ታዳሽ ኃይል በነዳጅ አምራቾች ላይ ያለውን ጥገኝነት ስለሚቀንሰው፣ በነዳጅ ምርት ላይ በከፍተኛ መጠን ጥገኛ የሆኑ ሀገራት የዲኦፖለቲካ ለውጥ ሊያጋጥማቸዎ ይችላል።
6)የቴክኖሎጂ ውስንነት
በታዳሽ ኃይል አጠቃቀም ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ውስንነት። ሊያጋጥም ይችላል