ከነዳጅ እና ነዳጅ አልባ ኢኮኖሚ የትኛው የተረጋጋ ነው?
ከነዳጅ (ኦይል) እና ነዳጅ አልባ(ነንኦይል) የራሳቸው ባህሪ ያሏቸው የኢኮኖሚ አይነቶቾ ናቸው
የነዳጅ ኢኮኖሚ በፔትሮሊየም እና ከፔትሮሊየም የተዛመዱ ምርቶችን በማምረት እና በመሸጥ ላይ የተመሰረተ ነው
ከነዳጅ (ኦይል) እና ነዳጅ አልባ(ነንኦይል) የራሳቸው ባህሪ ያሏቸው የኢኮኖሚ አይነቶቾ ናቸው።
ይህ ንጽጽር በሁለቱ ኢኮኖሚዎች መካከል ያለውን ቁልፍ የሚባሉ ልዩነቶች ግልጽ የማድረግ አላማ አለው።
የነዳጅ ኢኮኖሚ በፔትሮሊየም እና ከፔትሮሊየም የተዛመዱ ምርቶችን በማምረት እና በመሸጥ ላይ የተመሰረተ ነው። ከነዳጅ የሚገኘው ገቢ ትልቁን የጠቅላላ ሀገር ውስጥ ገቢ ወይም የጂዲፒ ድርሻ ይሸፍናል።
ነዳጅ አልባ ኢኮኖሚዎች ደግሞ ገቢያቸው ከተለያየ ምንጭ ስለሚሆን የተረጋጋ የኢኮኖሚ አፈጻጸም ይኖራቸዋል።
ይህ አይነት ኢኮኖሚዎች በሸቀጦች ዋጋ ለሚፈጠሩ ድንገተኛ ለውጦች ተጋላጭነቱ ዝቅ ያለ ነው።
በነዳጅ ላይ የተመሰረቱ ኢኮኖሚዎች ከነዳጅ ውጭ ኢኮኖሚያቸውን ለማስፋት የሚቸገሩ ሲሆን ነዳጅ አልባ ኢኮኖሚዎች ደግሞ ለጂዲፒያቸው አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብዙ ዘርፎችን ይዘዋል። ይህ የኢኮኖሚ አይነት ውጫዊ የኢኮኖሚ ችግሮችን መቋቋም ይችላል።
ባለነዳጅ ኢኮኖሚዎች በቂ የሚባል ገቢ ስለሚያገኙ በመሰረተልማት ግንባታ ላይ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያፈሱ ሲሆን ነዳጅ አልባ ኢኮኖማዎች በአንጻሩ መሰረተ ልማት ለመገንባት የግል እና የህዝብ ተሳትፎን ይጠይቃሉ።
ከአካባቢ ብክለት አንጻር ሲታይ ደግሞ የነዳጅ ኢኮኖሚዎች ከፍተኛ ብክለትን ያሳድራሉ።
ከነዳጅ ሽያጭ በሚገኝ ገቢ ላይ ጥገኛ የሆኑ መንግስታት፣ የነዳጅ ዋጋ በሚቀንስበት ጊዜ ችግር ውስጥ ይገባሉ። ነዳጅ አልባ የሆኑ ኢኮኖሚዎች የገቢ ምንጫቸው ሰፊ ስለሚሆን የተረጋጋ የፊስካል ፖሊሲ ይናኖራቸዋል።