ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የ738.2 ሚሊየን ዶላር ብድር ሰጠች
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያና በደቡብ ሱዳን መካከል የተደረገውን የብድር ሰምምነት አጽድቋል
በ10 ዓመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድሩ አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ ይሆናል
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የ738 ሚሊየን 226 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ብድር ሰጠች።
የኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባው የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
ምክር ቤቱ ካጸደቃቸው ረቂቅ አዋጆች መካከል የኢትዮጵያ መንግሥት ለደቡብ ሱዳን 738 ሚሊየን 264 ሺህ 159.94 የአሜሪካ ዶላር ብድር ለማቅረብ ያደረገውን ስምምት አንዱ ነው።
ብድሩ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን በመንገድ ለማስተሳሰር የሚውል ሲሆን በዋናነትም ከኢትዮጵያ ድንበር አንስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን እስከ 220 ኪሎ ሜትር የሚዘልቅ ነው።
ስምምነቱ የአምስት አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ10 ዓመት የሚመለስ ሲሆን፤ የ4 በመቶ ወለድ የሚታሰበብት መሆኑ ተጠቅሷል።
ብድሩ የሚመለሰው ባከሽ ወይም በድፍድፍ ነዳጅ ሲሆን፤ ተበዳሪው አገር በድፍድፍ ነዳጅ የሚመልስ ከሆነ በራሱ ወጪ እስከ ፖርት ሱዳን ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።
የብድር ስምምነቱ በሚመለስበት ወቅት የነዳጅ ዋጋ ለውጥ ቢኖር እንዴት ይታያል? ነዳጁ እስከ ፖርት ሱዳ ብቻ ለምን ሆነ ሌሎች አማራጭ ፖርቶች ለምን አልታዩም? የሚሉ ጥያቄዎች ከምክር ቤት ባላት ቀረርበዋል።
የግዘብ ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በሰጡት ምላሽ፤ የብድርሰ ስምምነቱ በዶላር መሆኑን ጠቅሰው፤ ብድሩ የተቀመጠው በድፍድፍ ነዳጅ በርሜል ቁጥር ሳይሆን በዶላር በመሆኑ፤ በብድሩ መመለሻ ጊዜ ላይ ተሰልቶ በሚመጣው መጠን የሚመለስ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ወደብን በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄም ጠቃ መሆኑን ጠቅሰው፤ ስምምነቱ በፈረመነት ወቅት የተቀመጠው ፖርት ሱዳን ነው፤ ነገር ግን ወደ ተፈጻሚነት ሲገባ እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች ወደቦችን መጠቀም ይቻላል ብለዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት እና በደቡብ ሱዳን መካከል የተደረገውን የብድር ሰምምነት ስምምት በአንድ ድምጸ ታዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ከዓለም አቀፉ የግንዘብ ድርጅት ብድር መውሰዷ የሚታወስ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር ላይም የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለኢትዮጵያ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ማጽደቁ ይታወሳል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ያጸደቀው የ4 ዓመት የተራዘመ ብድር አገልግሎት መሆኑም አይዘነጋም።