የዓለም ሀገራት ብድር ከጥቂት ቀናት በኋላ ከ100 ትሪሊዮን ዶላር ያልፋል ተባለ
አሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ ሌሎችም ሀገራት ከፍተኛ ብድር ያለባባቸው ሀገራት ናቸው
የዓለም ሀገራት ለፖለቲካ ስራዎች የሚያወጧቸው ወጪዎች እየጨመሩ መጥተዋል ተብሏል
የዓለም ሀገራት ብድር ከጥቂት ቀናት በኋላ ከ100 ትሪሊዮን ዶላር ያልፋል ተባለ፡፡
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ባወጣው ሪፖርት በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ የዓለም ሀገራት ያለባቸው ጠቅላላ ብድር 100 ትሪሊዮን ያልፋል ብሏል፡፡
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ አሁን ላይ የሀገራት ብድር የዓመታዊ ምርት መጠናቸውን የ92 በመቶ ድርሻ አለው፡፡
ከሶስት ዓመት በኋላ የሀገራት ጠቅላላ ብድር ከዓመታዊ ምርት መጠናቸው ብልጫእንደሚኖረው ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
የዓለማችን ቀዳሚ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው አሜሪካ እና ቻይና ያለባቸው የብድር መጠን ከፍተኛ መሆኑ ለዓለም ኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ምክንያት እንደሚሆንም አይኤምኤፍ በሪፖርቱ ላይ አስታውቋል፡፡
ብድር ለማግኘት የሞተ ሰው ወደ ባንክ የወሰደችው ብራዚላዊት ተያዘች
ከአሜሪካ እና ቻይና በመቀጠልም ብራዚል፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የብድር መጠን ካለባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ተጠቅሰዋል፡፡
ሀገራት ለፖለቲካ ፍላጎቶች ማስፈጸሚያ የሚያወጧቸው ወጪ እየጨመረ መምጣት ለሀገራት ብድር መጨመር ትልቁ ምክንያትም ነው ተብሏል፡፡
የዓለማችን ሀገራት ብድር መጠን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ከፍተኛ ደረጃ ለይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ቀስ በቀስ ሲቀንስ ቆይቷል፡፡
አሜሪካ አሁን ላይ ያለባት እዳ መጠን 35 ነጥብ 4 ትሪሊዮን የደረሰ ሲሆን ከቀናት በኋላ በሚካሄደው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ ግብር ለመቀነስ ቃል መግባታቸው የሀገሪቱ ብድር መጠን እንዲጨምር ሊያደርግ እንደሚልም አይኤምኤፍ አስታውቋል፡፡
በርካታ የዓለማችን ሀገራት ባለባቸው የብድር ጫና ምክንያት ተጨማሪ ገንዘብ ከህዝቡ በግብር መልኩ ለመሰብሰብ የህግ ማሻሻያዎችን እያደረጉ ናቸውም ተብሏል፡፡
የመንግስት ወጪ እየጨመረ መምጣት፣ ለፖለቲካ ስራዎች እና ኢኮኖሚውን የማያነቃቁ ስራዎች መስፋት ለሀገራት ብድር መጨመር ገፊ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡