የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እና ብድር አጸደቀ
ገንዘቡ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል ነው
የዓለም ባንክ ካተደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊየን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ ነው
የዓለም ባንክ የዳይሬክቶች ቦርድ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እና ብድር ማጽደቁን ባንኩ አስታወቀ።
የዓለም ባንክ ዛሬ ምሽት በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫው የገንዘብ ድጋፍና ብድሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን አስታውቋል።
በዚህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው ባኩ፤ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የተራዘመ ብድር ነው ብሏል።
የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት፦
1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ስጦታ
500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ እንዲራዘም፤
320 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር
1 ነጥብ 15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
6 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለበጀት ድጎማ
2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂ ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር እንደምታገኝ ተገልጿል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) ስራ አስፍጻሚ ቦርድ በትናትናው እለት ለኢትዮጵያ የአራት ዓመት የ3.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን ማጽቁ ይታወሳል።
የተቋሙ ቦርድ ትናንት ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል መሆኑንም አስታውቋል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የስራ አስፍጻሚ ቦርድ ቦርድ ብድሩን ያጸደቀው የኢትዮጵያ መንግስት በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ትናነት ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ ነው።