የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ለኢትዮጵያ የ3.4 ቢሊዮን ዶላር ብድር አጸደቀ
የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ዛሬ ያጸደቀው የ4 ዓመት የተራዘመ ብድር አገልግሎት መሆኑ ተገልጿል
1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ የሚለቀት መሆኑ ተመላቷል
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) ስራ አስፍጻሚ ቦርድ ለኢትዮጵያ የአራት ዓመት የ3.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተራዘመ ብድር አገልግሎት አቅርቦትን አጸደቀ።
የተቋሙ ቦርድ ዛሬ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር አካባቢ የሚሆን ገንዘብ ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ የሚያስችል መሆኑንም አስታውቋል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.ኤም.ኤፍ) የስራ አስፍጻሚ ቦርድ ቦርድ ብድሩን ያጸደቀው የኢትዮጵያ መንግስት በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት ዛሬ ሰኞ ተግባራዊ ማድረጉን ተከትሎ ነው።
አይ ኤም ኤፍ አሊትዮጵያ ያጸደቀው ብድር ማዕቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለሶችን ለመፍታት፣ የውጪ እዳ [አከፋፈል] ዘላቂነትን በመመለስ እንዲሁም ለላቀ አካታች ለሆነ እና በግል ዘርፉ ለሚመራ እድገት መሠረትን በመጣል የመንግሥትን ‘ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ’ አጀንዳ የሚደግፍ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት ከልማት አጋሮች እና አበዳሪዎች የሚገኝ ተጨማሪ የውጪ የገንዘብ አቅርቦትን እንደሚያፋጥን ይጠበቃል።
በአራት ዓመቱ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦት የሚደገፈው የመንግሥት የኢኮኖሚ ፕሮግራም የግል ዘርፉን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ ሁለገብ የፖሊሲ ፓኬጅን እንዲሁም የላቀ እና በይበልጥ አካታች የሆነ እድገትን ማምጣትይቻል ዘንድ ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግን ኢላማው ያደረገ ነው።
ማሻሻያው ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች/አባዎራዎች ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ለማለዘብ ይቻል ዘንድ የማህበራዊ ሴፍቲ ኔቶችን ማጠናከርም የመንግሥት የማሻሻያ ፕሮግራም አንድ ወሳኝ ክፍለአካል ነው። ቁልፍ የሚባሉት ፖሊሲዎችም የሚከተሉትን ያካትታሉ፡
1) ውጫዊ ኢሚዛናዊንትን ለመፍታት እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን ለማስታገስ በገበያ ወደሚወሰን የምንዛሪ ዋጋ መሄድ፤
2) የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍን በማዘመን የዋጋ ግሽበትን መዋጋት፤
3) የሀገር ውስጥ የገንዘብ ምንጮችን በማሰባብሰብ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ሕዝባዊ ወጪዎች ማዋል፤
4) ከውጪአበዳሪዎች ጋር የሚደረጉ ወቅታዊ የእዳ ሪስትረክቸሪንግ ስምምነቶችን በመፈጸም ጭምር የእዳ አከፋፈል ዘላቂነትን መመለስ እንዲሁም
5) ወሳኝ የሆኑ የማክሮ ፋይናንሺያል ተጋላጭነቶችን ለመቀነስ የመንግሥት ኢንተርፕራይዞችን የገንዘብ አቋም ማጠናከር።
ፕሮግራሙ ከልማት አጋሮች የሚገኝ ተጨማሪ የገንዘብ አቅርቦትን በማፋጠን እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያለው የእዳ ሪስትረክቸሪንግ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚያደርግ ማዕቀፍ በመስጠት ረገድ እንደሚያግዝ ይጠበቃል።