የደመራ በዓል አከባበር በምስል
በዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከ6 ሺህ በላይ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪ ወጣቶች ዝማሬ አቅርበዋል

የደመራ በዓል መስቀሉን ለማግኘት ንግስት ኢሌኒ ፍላጋ ያስጀመሩበት ሰለሆነ በአማኞች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ነው
ልየመስቀል ደመራ በዓል በዛሬው እለት ተከብሮ ውሏል።
በዓሉ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤት ክርስቲያን ብጹአን አባቶች፣ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ተከብሯል።
በዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ከ6 ሺህ በላይ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪ ወጣቶች ዝማሬ አቅርበዋል።
የደመራ በዓል መስቀሉን ለማግኘት ንግስት ኢሌኒ ፍላጋ ያስጀመሩበት ሰለሆነ በአማኞች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው ሀይማኖታዊ በዓል ነው።
የደመራ በዓል ከመስቀል አደባባይ ባሻገር ምእመናን በየቤተክርስቲያቱና በቤታቸው ደመራ በመለኮስ ያከብሩታል።
የመስቀል ደመራ በዓል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ በተጨማሪ ባሉት ባህላዊ ትእይንቶቹ በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።