ናዚን በይፋ ያወደሱት የካናዳ ፖርላማ አፈጉባዔ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ገለጹ
የአፈጉባኤው ንግግር ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት ምክንያታዊ እንድታደርግ ይረዳታል ተብሏል
ድርጊታቸው ቁጣ ማስነሳቱን ተከትሎ ሮታ ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል
የካናዳው ሃውስ ኦፍ ኮመንስ አፈጉባዔ አንቶኒ ሮታ የቀድሞ የናዚ ተዋጊን በፖርላማ ፊት ካወደሱ ከጥቂት ቀናት በኋላ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ተናግረዋል።
የአፈጉባኤው ንግግር ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጦርነት ምክንያታዊ እንድታደርግ ይረዳታል ተብሏል።
አፈጉባዔ ሮታ እንደገለጹት ለዩክሬን ኘሬዝደንት ዘለንስኪ ክብር ለመስጠት በተጠራው የፖርላማ ስብሰባ ላይ የቀድሞ የተዋጊውን ያርሶላቭ ሁንካን መጋበዛቸው ስህተት ሰርተዋል።
ሮታ ሁንካን በአደባባይ ጀግና ሲሉ እውቅና ሰጥተዋል።
ሁንካ በሁለኛው የአለም ጦርነት ወቅት በናዚ አንድ ክፍለጦር ውስጥ ተሰልፎ የተዋጋ መሆኑ ሲታወቅ አፈጉባዔው ንግግራቸውን መከላከል የማይችሉበት ደረጃ ሊደርሱ ችለዋል።
ሩሲያ ክስተቱን እጅግ አደገኛ ነው ብላለች።
የአፈጉባዔው ይፋዊ የሆነ እውቅና በካናዳ ያሉትን ጨምሮ በመላው አለም ያሉትን የጀዊሽ ማህበረሰቦችን አስቆጥቷል።
ድርጊታቸው ቁጣ ማስነሳቱን ተከትሎ ሮታ ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል። ከዚህ በጨማሪም ንግግራቸው ለሚያስከትለው ችግር ኃላፊነት እንደሚወስዱ እና ስልጣናቸውንም እንደሚለቁ ይፋ አድርገዋል።
በካናዳ የሩሲያ አምባሳደር ኦሌግ ስቴቫኖቭ የአፈጉባኤውን ንግግር በመቃወም ለጠቅላይ ሚኒስትር ቱሪዶ ደብዳቤ ጽፈዋል።