የፈረንሳይ አምባሳደር ኒጀርን ለቀው ወጡ
ፈረንሳይ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝደንት መሀመድ ባዙም ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ስትወተውት ቆይታለች
አምባሳደሩ መፈንቅለ መንግስት ያደረገው ወታደራዊ ጁንታ ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቃቸው ከአንድ ወር በኃላ በዛሬው እለት መውጣታቸው ተገልጿል
በኒጀር የፈረንሳይ አምባሳደር ሲልቪያን ኢቴ መፈንቅለ መንግስት ያደረገው ወታደራዊ ጁንታ ለቀው እንዲወጡ ካስጠነቀቃቸው ከአንድ ወር በኃላ በዛሬው እለት መውጣታቸው ተገልጿል።
አምባሳደሩ የወጡት የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ ፈረንሳይ ዲፕሎማቶቿን እና ወታደሮቿን እንደምታስወጣ ከተናገሩ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
በፈረንሳይ እና በቀድሞ ቀኝ ግዛቷ ኒጀር መካከል ያለው ግንኙነት ባለፈው ሐምሌ ወር መፈንቅ መንግስት መካሄዱን ተከትሎ ችግር ውስጥ ወድቋል።
አምባሳደሩ የኒጀርን ጥቅም በሚጎዳ ተግባር ተንቀሳቅሰዋል ያለው ወታደራዊ ጁንታ ባለፈው ነሐሴ ወር በ48 ሰአታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።
በወቅቱ ፈረንሳይ ይውጡ የሚለውን ትዕዛዙ ውድቅ አድርጋ የነበረ ቢሆንሞ ማክሮን እሁድ እለት አምባሳደሩ ወደ ፖሪስ እንደሚመለሱ አስታውቀዋል።
ፈረንሳይ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝደንት መሀመድ ባዙም ወደ ስልጣን እንዲመለሱ ስትወተውት ቆይታለች።
ሮይተርስ ሁለት የደህንነት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው አምባሳደሩ ከሀገር ወጥተዋል።
ኒጀርን ጨምሮ በሌሎች የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ሀገራት የጸረ-ፈረንሳይ እንቅስቃሴዎች እየተስፋፉ ነው።