ኢትዮጵያ ላለባት የቻን ማጣርያ ለተጫዋቾች ጥሪ አደረገች
ቻን በሀገር ውስጥ ሊግ በሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚዋቀሩ ብሄራዊ ቡድኖች መካከል ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ነው
የ2023 አፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል
በሀገር ውስጥ ሊግ በሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚዋቀሩ ብሄራዊ ቡድኖች መካከል ለሚካሄደው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን)ውድድር ማጣርያ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አደረጉ።
በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በጥር 2023 የሚካሄደውን የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ውድድር ማጣርያ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቅድመ ማጣሪያውን ከደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያካሂዳል።
የቅድመ ማጣያ ጨዋተዎቹም ሐምሌ 15 እና ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በታንዛንያ እንደሚካሄድ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚሀም መሰረት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቀጥሎ ለተዘረዘሩ ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
ግብ ጠባቂዎች
ፋሲል ገ/ሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ) ፣ በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አላዛር ማርቆስ (ጅማ አባጅፋር)
ተከላካዮች
ሱሌማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና) ፣ ያሬድ ባየህ (ፋሲል ከነማ) ፣ ሚሊዮን ሰለሞን (አዳማ ከተማ) ፣ ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አስራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ)
አማካዮች
አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ከነአን ማርክነህ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) ፣ በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ) ፣ መስኡድ መሐመድ (ጅማ አባ ጅፋር)
አጥቂዎች
ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ዳዋ ሁቴሳ (አዳማ ከተማ) ፣ ብሩክ በየነ (ሀዋሳ ከተማ) ፣ በረከት ደስታ (ፋሲል ከነማ) ፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና) ናቸው።