የትስስር ገጾቹ መዘጋት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ተነግሯል
በኢትዮጵያ በኃይማኖት ውጥረት ሳቢያ መንግስት የማህበራዊ የትስስር ገጾችንና የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎችን ገድቧል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የካቲት አምስት የሚያደርገውን ሰልፍ መንግስት መከልከሉን እንደማይቀበል ባሳወቀ በሰዓታት ውስጥ እንደ ፌስቡክ ያሉ የማህበራዊ የትስስር ገጾች ተገድበዋል።
ኔትብሎክ የተሰኘው የበይነ-መረብ አገልግሎት ተከታታይ ድርጅት ሀሙስ የካቲት ሁለት በኢትዮጵያ የፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ መድረኮች የአውታር መረጃዎችን ተመመርኩዞ እገዳ ተጥሎባቸዋል ብሏል።
ድርጊቱ የተፈጸመውም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት መንግስትን ተቃዋሚ ሰልፍ ለማድረግ በታሰበበት ወቅት ነው ብሏል።
ፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ቲክቶክ "በመንግስታዊው የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም ተገድበዋል" በማለትም አክሏል።
ኢትዮጵያ በተቃውሞና አለመረጋጋቶች ወቅት የማህበራዊ ትስስሮች የእገዳ ሰፊ ታሪክ አላት።
ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በቅርቡ ዓለም አቀፍ የበይነ-መረብ አስተዳደር ጉባኤን ብታስተናግድም፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ "በይነ-መረብ ውሃ ወይም አየር አይደለም" በማለት አለመረጋጋት ካለ ሊዘጋ እንደሚችል መናገራቸው አይዘነጋም።