ተ.መ.ድ. የኢትዮጵያው የኢንተርኔት መዘጋት ያሳስበኛል አለ
በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ አስፋላጊውን መረጃ ለመቀያየር የኢንተርኔት መኖር አስፋላጊ ነው-ቃል አቀባይዋ ሩፔርት ኮለቪል
ተመድ በተወሰነ የኢትዮጵያ ክፍል ያለው የኢንተርኔት መዘጋት ያሳስበኛል አለ
ተመድ በተወሰነ የኢትዮጵያ ክፍል ያለው የኢንተርኔት መዘጋት ያሳስበኛል አለ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ሩፔርት ኮለቪል በተወሰነ የኢትዮጵያ ክፍል ያለው የግንኙነት መቋረጥ (ኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት) ሰዎች ስለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅታዊ መረጃ እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡
ቃል-አቀባይዋ ሁሉም ሀገራት የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎትን በማዳረስ የኮሮና ወረርሽኝን መከላከለ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ሁሉም ሰው መረጃ የማግኘት መብት አለው ያሉት ቃል-አቀባይዋ የኢትዮጵያ መንግስት ባስቸኳይ የኢንተርኔትና የስልክ ማቋረጥን ማቆም አለበት ብለዋል፡፡ ባለስልጣናት፣ የጤና ባለሙያዎችንና የሚመለከታቸው አካላት በወረርሽኙ ዙሪያ አስፋላውን መረጃ ለመቀያየር የኢንተርኔት መኖር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች በፀጥታ ችግር ምክንያት የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ያነሳው ተመድ፣ ይህ የግንኙነት መቋረጥ የግንዛቤ ስራዎችን ለመስራት አዳጋች እንደሚሆንና እንደሚያሳስባቸው ሩፔርት ኮለቪል ገልጸዋል፡፡
ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ኢንተርኔት ብቸኛው አማራጭ አለመሆኑን በመጠቆም በራዲዮ፣በቴሌቪዠንና በሰው በሰው መረጃ ማግኜት አንደሚቻል ገልጸዋል፡፡