የአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት( ዳታ) ዛሬ ተለቋል
የአርቲስት ሀጫሉ ግድያ ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት( ዳታ) ዛሬ ተለቋል
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ድንገተኛ ግድያ ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት(ዳታ) ከዛሬ ጀምሮ መለቀቁ ታውቋል፡፡
ግድያውን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ከሳምንት በፊት “የብሮድባንድና የዋይፋይ” አገልግት በአዲስ አበባ ከተማ መስራት መጀመሩ ይታወሳል፡፡
መንግስት በአርቲስቱ ግድያ ተሳትፈዋል ያላቸውን ተጠርጣሪዎችንም መያዙን አስታውቋል፡፡
ከአርቲስቱ ግድያ በኋላ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረ ብጥብጥ ከ239 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በርካት የንግድ ተቋማትም ውድመት ደርሶባቸዋል፡፡
መንግስት በብጥብጡ ተሳትፈዋል ያላቸውን ግለሰቦች መያዛን በተለያየ ጊዜ አስታውቋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ጌታቸው ባልቻ በኦሮሚያ ክልል በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የተጠረጠሩ ከ7100 በላይ ግለሰቦች በፖሊስ መያዛቸውን ለአል ዐይን አማርኛ ባለፈው ሳምንት ገልጸው ነበር፡፡