በሱዳን ኢንተርኔት የተቋረጠው ወታደራዊ መሪው አልቡርሃን መንግስት ማፍረሳቸውን ከሳወቁ በኋላ ነበር
በሱዳን በተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት መመለሱን የሱዳን ዜና አገልግሎት ሱና ዘግቧል፡፡
በሀገሪቱ ኢንተርኔት የተቋረጠው፤ የሱዳን ወታደራዊ ኃይል የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ከስልጣን በማውረድ ቁም እስረኛ ማድረጉን ተከትሎ በተፈጠረው ሀገርአቀፍ ተቃውሞ ነበር፡፡
በፈረንጆቹ ጥቅምት 25፣ የሱዳን ወታደር ኮማንድ አዛዠ የሆኑት ጄነራል አልቡርሃን የሱዳን መንግስትንና ይመሩት የነበረው ሉአላዊ የሽግግር ምክርቤት ማፍረሳቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል፡፡
በፈረንጆቹ ህዳር 9፣ የሱዳን ፍ/ቤት የኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች የኢንተርኔት አገልግሎት በአስቸኳይ እንዲያስታወቁ አዟል፡፡
በሱዳን ከትናንት በስቲያ በተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ህዝባዊ ተቃውሞ፤ የሱዳን ወታደር ከ15 በላይ ንጹሃንን መግደላቸውንና በርካቶችን ማቁሳቸውን ተዘግቧል፡፡ መንግስት የኢንትርኔት አገልግት ያቋረጠውም፣ ህዝቡ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም እንዳይሰባሰብ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡
ወታደራዊ አመራሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክን የቁም እስረኛ ካደረገ በኋላ ድርድር እንዲደረግ ሙከራ የተደረገ ቢሆንም፤ድረድሩ ወጤታማ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
መፈንቅለ መንግስት አድራጊው የሱዳን ጦር መሪ ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አዲስ ሉዓላዊ ምክር ቤት ማቋቋማቸው ይታወሳል፡፡ቡርሃን ምክር ቤቱን ያቋቋሙት በመፈንቅለ መንግስቱ የፈረሰውን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ለመተካት ነው፡፡
አዲስ የተመሰረተው ምክር ቤት 15 አባላት ያሉት ሲሆን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤቱን ሲመሩት የነበሩት ቡርሃን ራሳቸውን የአዲሱ ምክር ቤት መሪ አድርገው ሾመዋል፡፡