የኢትዮጵያ መንግስት በጅምላ ተቀብረው ስለተገኙ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ከማላዊ መንግስት ጋር እየተወያየ መሆኑን አስታወቀ
25 ኢትዮጵያዊያን በማላዊ በአንድ ስፍራ ተቀብረው ተገኝተዋል መባሉ ይታወሳል
የማላዊ መንግስት ኢትዮጵያዊያኑ በህገወጥ ሰዎች አዘዋዋሪ ሰላባ ሳይሆኑ አይቀሩም ብሏል
በጅምላ ተቀብረው ስለተገኙ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ከማላዊ መንግስት ጋር እየተወያየ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።
ይህ አስከሬን በማላዊ ልዩ ቦታው ምዚምባ በተባለ ቦታ መገኘቱን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።
አስከሬኖቹ የተገኙበት ስፍራ ከማላዊ ዋና ከተማ ኢሎንግዌ 250 ኪሎሜትር ርቃት ላይ እንደሆነም የማላዊ ፖሊስ ገልጿል።
ኢትዮጵያዊያን ናቸው ተብሎ የተጠረጠረው ይህ የጅምላ መቃብር የተገኘው የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ መጠቆማቸውን ተከትሎ ነው።
የማላዊ ፖሊስም ከትናንት በስቲያ አደረኩት ባለው ምርመራ እድሜያቸው ከ20 እስከ 40 የሚሆኑ ሰዎች በጅምላ በአንድ ስፍራ ተቀብረው ማግኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንሳስታወቀው በማላዊ በአንድ ስፍራ ተቀብረው ተገኝተዋል ስለተባሉ 25 ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከማላዊ መንግሥት ጋር እየመረመረ መሆኑን አስታውቋል።
እንደ ማላዊ ፖሊስ ጥርጣሬ መረጃ ከሆነ ተቀብረው የተገኙት ዜጎች ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ነገር ግን ማን እንደገደላቸው ምርመራው መቀጠሉን ገልጿል።