በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት በተቀሰቀሰ ግጭት በ2 ቀን ውስጥ ከ150 በላይ ሰዎች ሞቱ
በብሉ ናይል ግዛት የጎሳ ግጭት የህጻት እና የሴቶች ህይወት አልፋል
በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ከመሬት ጋር በተያያዘ የጎሳ ግጭት ተቀስቅሷል
በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት በተቀሰቀሰው እና ሁለት ቀናትን ባስቆየጠረው የጎሳ ግጭት በትንሹ የ150 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
በስዳን ደቡባዊ በሉ ናይል ግዛት ከመሬት ጋር በተያያዘ የጎሳ ግጭት ከተቀሰቀስ ሁለት ቀናትን ማስቆጠሩ ተነግሯል።
የዋድ አል ማሂ ሆስፒታል ኃለፊ አባስ ሙሳ፤ በግጭቱ 150 ሰዎች መሞታቸውን እና ከእነዚህም መካከል ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል ሲሉ አስታውቀዋል።
ከሞቱት በተጨዋሪም 86 ሰዎች መቁሰላቸውን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
በብሉ ናይል ግጭት የተቀሰቀሰው ባለፈው ሳምንት በሃውሳ ህዝቦች እና በተቀናቃኝ ቡድኖች መካከል በመሬት ጉዳይ ላይ አለመግባባት ከተስተዋለ በኋላ መሆኑ ተነግሯል።
ተፈጠረው አለምግባባትን ተከትሎ የተኩስ እሩምታ መከፈቱ እና ቤቶች መቃጠላቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከፍተኛ ነዋሪዎች ከኖሪያቸው እንደሸሹ ተዘግቧል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት መሰረት እስከ ማክሰኞ ድረስ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ቃጠሎውንና ዘረፋውን ሸሽተው ተፈናቅለዋል።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሱዳን እየተስተዋለ የመጣው ጎሳ ግጭት ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ ኪሳራ ከማስከተሉም ለዴሞክራሲያዊ ሽግግርና ለሰላም ሂደቱ አንዱ ጠንቅ እንደሆነ ይነገራል።
በርካቶችም የጎሳ ግጭት ሱዳን የምትታመምበት መቅሰፍት ነው ሲሉ ይደመጣሉ፡፡