ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ከታገዱ ምርቶች መካከል ዋነኞቹ የትኞቹ ናቸው…?
ምርቶቹ እንዳይገቡ የታገዱት የህገወጥ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን ለመቆጣጠር እንደሆነ ባንኩ አስታውቋል
የቤት መኪናን ጨምሮ 38 የተለያዩ ምርቶች ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ዕገዳ መጣሉን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ
የቤት አውቶሞቢልን ጨምሮ 38 አይነት የተለያዩ ሸቀጦች ላልተወሰነ ጊዜ ወደ አገር እንዳይገቡ የባንክ መተማመኛ ሰነድ (LC) እንዳይከፈትላቸው ውሳኔ ማለፉን ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።
የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና ዋና ኢኮኖሚስት አቶ ፍቃዱ ድጋፌ እንዳስታወቁት፤ የተመረጡት ሸቀጦች ለይስሙላ በአነስተኛ የገንዘብ መጠን LC ተከፍቶላቸው የሚገቡ ናቸው ብለዋል።
የአስመጪዎቹ የውጭ ምንዛሬ ዋነኛ ምንጫቸው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያው እና ህገ ወጥ ኃዋላ ነው ያሉ ሲሆን፤ በመሆኑም ምርቶቹ እንዳይገቡ መከልከሉ የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን እንደሚያወርደው ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።
ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ከታገዱ ምርቶች መካከል ዋነኞቹ
1. የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች እና ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች (በኤሌክትሪክ ሞትር የሚሰሩትን ሳይጨምር)
2. የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎች (በኤሌክትሪክ ሞትር የሚሰሩትን ሳይጨምር) እና ብስክሌቶች
3. ከረሜላዎች ማስቲካዎች፣ ቸኮሌት፣ ብስኮቶች እንዲሁም ዋፈሮች
4. የፍራፍሬ ጫማቂ እና የታሸጉ ፍራፍሬዎች አንዲሁም ከፍራፍሬ የተዘጋጁ ጃሞች እና የድንች ጥብሶች
5. ውስኪ፣ ወይን፣ ቢራ እና ሌሎች የመጠጥ አልኮሎች እንዲሁም ሲጋራ
6. የሰው (ሁማን) እና ሰው ሰራሽ ፀጉር (ዊግ)፣ የውበት መጠበቂያዎች፣ ሽቶ፣ ሳሙናዎች፣ እንዲሁም ቦርሳና ዋሌት
7. የገበታ ጨው፣ የዶሮ ስጋ፣ የአሳማ ስጋ፣ ቱናዎች፣ ሰርዲኖች እና ሌሎች የአሳ ምርቶች
8. የእጅ፣ የግድግዳ እና የጠረጴዛ ሰዓቶች፣ ዣንጥላዎች እና ምንጣፎች ይገኙበታል