በኢትዮጵያ በብዛት የሚዘወተረው ቶዮታ መኪና በሀገር ውስጥ እንዲገጣጠም ጥያቄ ቀረበ
ቶዮታ ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ አውቶሞቢል መገጣጠም ላይ እንዲሰማራ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርቧል
የቶዮታ ኩባንያ ጥቄውን በመቀበል በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማደረግ ፍላጎት አሳይቷል
በኢትዮጵያ በብዛት የሚዘወተረው ቶዮታ መኪና በሀገር ውስጥ እንዲገጣጠም ጥያቄ መቅረቡን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
በኢንዱስትሪ ሚኒስትር በአቶ መላኩ አለበል የሚመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ አመራሮች የልዑካን ቡድን ወደ በጃፓን ጉብኝት ማድረጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።
ልዑካን ቡድኑ በጃፓን ሀገር ከሚገኙ የልማት አጋሮች ጋር ውይይቶች እና የተቋማት ጉብኝት ተደርጓል።
በዚህም የቶዮታ ኩባያን የጎበኙ ሲሆን፤ ከኩባያው አመራሮች ጋር መወያየታቸውንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በውይይቱም ቶዮታ ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርግ በተለይም አውቶሞቢል መገጣጠም ላይ እንዲሰማራ በኢንዱስትሪ ሚኒስትር በአቶ መላኩ አለበል ጥያቄ ቀርቦለታል።
የቶዮታ ኩባያም ከኢትዮጵያ የቀረበለትን ጥያቄ በመቀበል ኢንቨስት ለማደረግ ፍላጎት እንዳለው ማሳየቱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
በሌለ በኩል የቶዮታ ኩባንያ የአውቶሞብል የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስልጠናዎችን ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።
በኢንዱስትሪ ሚኒስትር በአቶ መላኩ አለበል የተመራው ልዑክ በቆይታው የጃፓን ምርታማነት ማዕከል (JPC)፤ የጃፓን ሳይንቲስቶች እና ማሃንዲሶች ማህበር (JUSE) እንዲሁም የቶዮታ ኩባንያ ተቋማት መጎብኘቱ ተገልጿል።