ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ የስፖርት ውድድር ስምንተኛ ሆና አጠናቀቀች
ግብጽ፣ ናይጀሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ከአንድ እስከ ሶተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል
ኢትዮጵያ በውድድሩ በ9 ወርቅ፣ በ8 ብር እንዲሁም በ5 ነሀስ በድምሩ በ22 ሜዳሊዎች ስምንተኛ ሆና አጠናቃለች
ኢትዮጵያ በመላው አፍሪካ የስፖርት ውድድር ስምንተኛ ሆና አጠናቀቀች፡፡
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋና መዲና አክራ ሲካሄድ የነበረው የመላው አፍሪካ ስፖርታዊ ውድድር ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ውድድር 47 ወንድ፣ 40 ሴት በድምሩ 87 አትሌቶችን ያሳተፈች ሲሆን ሰባት ወርቅ፣ 7 ብር እንዲሁም 4 ነሀስ በድምሩ 18 ሜዳልያዎችን ማግኘት ችላለች፡፡
በቦክስ ውድድር ደግሞ በሁለቱም ጾታዎች ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ስትገባ ቤተልሄም ገዛሀኝ በ52 ኪሎ እና ቤተልሄም ወልዴ በ66 ኪሎ ከሶስት አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ እንድታስመዘግብ አድርገዋል፡፡
ሌላኛው የቦክስ ተወዳዳሪ ነቃ ተመስገን በ75 ኪሎ የነሀስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ማስገኘቱ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ በአጠቃላይ በዚህ ውድድር ላይ በ9 ወርቅ፣ በ8 ብር እንዲሁም በ5 ነሀስ በድምሩ በ22 ሜዳሊዎች ስምንተኛ ሆና አጠናቃለች፡፡
ግብጽ በ99 ወርቅ፣በ46 ብር እንዲሁም በ42 የነሀስ ሜዳሊያ በድምሩ በ187 ሜዳሊያዎች ውድድሩን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፣ ናይጀሪያ በ47 ወርቅ፣ 33 ብር እና 41 የነሀስ ሜዳሊያዎች በድምሩ 121 ሜዳሊያዎች ሁለተኛ ስትሆን ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በ32 ወርቅ በ32 ብር እንዲሁም በ42 የነሀስ ሜዳሊያዎች በድምሩ 106 ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ ውድድሩን ሶስተኛ ሆና ማጠናቀቅ ችላለች፡፡
የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አሸናፊዎች ምን ያክል ገንዘብ ያገኛሉ?
ጉረቤት ሀገር ኬንያ በ8 ወርቅ በ7 ብር እንዲሁም በ20 የብር በድምሩ በ35 ሜዳሊያዎች 10ኛ ሆና ስታጠናቅቅ ሌላኛዋ ምስራቅ አፍሪካ ሀገር ኤርትራ ደግሞ በ7 ወርቅ በ2 ብር በ6 ነሀስ በድምሩ በ15 ሜዳሊያዎች 11ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች፡፡
በዚህ ውድድር ላይ ከተሳተፉ 50 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኙት ኢትዮጵያ ጨምሮ 28 ሀገራት ብቻ እንደሆኑ ከውድድሩ ማጠቃለኛ ሪፖርት ላይ ተመልክተናል፡፡